ሎካላይዝ የሚደረገውን ሶፍትዌር ማዘጋጀት

ሎካላይዜሽን ጠቃሚ ያልሆነ እና ብዙ ጊዜ የሚፈጅ ነገር ተደርጎ ይወሰዳል፣ በዚህም ምክንያት ብዙ ድርጅቶች ጊዜው እስኪረፍድ ድረስ ለጉዳዩ ቦታ አይሰጡትም። ሶፍትዌር አዘጋጆቹ ኮዱን ሲያዘጋጁ ለሌሎች ቋንቋዎች፣ ዓለም አቀፋዊ ቅርጾች ወይም ሌሎች አስፈላጊ የሎካላይዜሽን ክፍሎች ትኩረት ባለመስጠታቸው ምክንያት ወደፊት ሌሎች ቋንቋዎችን ለማካተት ሙሉ ፕሮጀትዎትን እንደገና ማስተካከል ሊኖርብዎት ይችላል።

ነገሮች ተበላሽተው ወደ ውድቀት ለማምራት ትንሽ ስሕተት በቂ ነው። በመነሻ ይዘቱ ላይ ያሉ ስህተቶች ቀድመው በአግባቡ ካልተስተካከሉ በተለያዩ ቋንቋዎች ሊደገሙ ብሎም የበለጠ ጎልተው ሊቀርቡ ይችላሉ። ከትርጉም በኋላ የሎካላይዜሽን ስህትቶችን በማረም ወራትን ማባከን ካልፈለጉ፣ ከመጀመሪያው ሶፍትዌርዎትን ዓለም አቀፋዊ ያድርጉ። ይህም ማለት በቀላሉ እና በመጠነኛ ሥራ አዳዲስ ቋንቋዎችን ወደ ሶፍትዌርዎት ማስገባት ይችላሉ ማለት ነው።

በቋንቋዎች መካከል ኮድ ማድረጉን አንድ ዓይነት መልክ ለመስጠት ሶፍትዌር አዘጋጆቹ ዩኒኮድ [Unicode (UTF-8)] ተግባራዊ ያደርጋሉ። ለሁሉም ፊደላት የተለየ ምልክት ይኖረዋል እንዲሁም ይህንን በዓለም ላይ ላሉ ሁሉም ቋንቋዎች ማለት ይቻላል መተግበር ይችላል። ውሂቡን ለእያንዳንዱ አዲስ ቋንቋ ማስማማት ይችሉ ዘንድ፣ ፕሮግራመሮቹ የመነሻውን ይዘት ኮድ ከተተረጎሙት ስትሪንጎች ለይተው ለወደፊት ጥቅም ያስቀምጧቸዋል። ይህ ማለት በአጭሩ ወደ አዲስ ቋንቋ መተርጎም ሲፈልጉ ስትሪንጎቹን መከፋፈል አይኖርብዎትም። ሶፍትዌርዎትን ዓለም አቀፋዊ ማድረግ አካባቢ ላይ የተመሠረቱ ምርጫዎችን ለማድረግ ኮዶችን እንዲያስቀምጡ ያስችልዎታል፣ እነዚህ ኮዶችም የቁጥሮችን አቀማመጥ፣ ቀን፣ ሰዓት፣ መለኪያዎች እና ገንዘቦችን በቀላሉ ለመቀየር ይረዳሉ።

ASO/SEO ስትራቴጂ

ድር ጣቢያን እና የግብይት ሰነዶችዎን ሎካላይዝ ማድረግ SEO ሊያሻሽል ይችላል።    ስለ ደርጅትዎ የሞባይል መተግበሪያ ወይም ስለ ሶፍትዌርዎት ስሪት ከሆነ እያሰቡ ያሉት፣ ASO በተመሳሳይ መልኩ መሠረታዊ ነው። ስለዚህ የሶፍትዌር ሎካላይዜሽኑ ከተጠናቀቀ በኋላ፣ የ SEO ስትራቴጂዎት ወጥ መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርብዎታል። ምንም እንኳን ብዙ ሰዎች ስለ SEO/ASO ስትራቴጂ ማሰብ የሚጀምሩት በፕሮጀክቶች መጨረሻ ላይ ቢሆንም ይህ ጉዳይ መታቀድ ያለበት ከፕሮጀክቱ መጀመሪያ ጀምሮ ነው። ለምን? ምክንያቱም በውጪ ቋንቋ የተዘጋጀውን ይዘት በትክክለኛዎቹ ቁልፍ ቃላት እና የፍለጋ ቃላት ተተርጉሞ እና ለተጠቃሚዎች ተመቻችቶ በይነ መረብ ላይ እና የመተግበሪያዎች መደብር ላይ መቅረብ ስላለበት ነው።

የእርስዎን ንግድ ሥራ ሊያሟሉ የሚችሉ ወይም ተዛማጅ PR እና link juice ሊያስተላልፉ የሚችሉ አገናኞችን ከአካባቢያዊ የድር ጣቢያዎች ወደ እርስዎ የድር ጣቢያ ማዘጋጀት ይኖርብዎታል። ሁሉም የሦስተኛ ወገን ድር ጣቢያ አገናኞች ወደ እንግሊዝኛው የድር ጣቢያዎት ስሪት የሚመሩ ከሆነ SEO ላይ ትልቅ ሥራ ይጠብቅዎታል። ፍለጋዎች በአብዛኛው አካባቢያዊ ነው እንዲሁም ደንበኞች ፍለጋ ሲያካሂዱ በአቅራቢያቸው ያሉት የበለጠ ተዛማጅ የሆኑ ውጤቶች ይመጡላቸዋል። በአካባቢው ያለን የስልክ ቁጥሮች፣ ገጾች እና ቢሮ (ካለዎት) በመጨመር ድር ጣቢያዎትን ሎካላይዝ ማድረግ የፍለጋ ፕሮግራም ውጤቶች ገጽ [(SERP) Search Engine Results Page] ላይ የሚኖርዎት ደረጃ ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ይረዳዎታል። ከመተግበሪያዎች መደብር ጋር ከፍተኛ ተመሳሳይነት አለው። በጥሩ ሁኔታ የተሠራ መተግበሪያ ወደ ፈረንሳይኛ ቋንቋ ሎካላይዝ አድርገው ከሆነ፣ ቁልፍ ቃላቱን በትክክል ካላስቀመጡ ሎካላይዝ መደረጉ ብቻ ምንም አይጠቅምዎትም። በውድድሩ ውስጥ በቀላሉ ጎልተው ሊታዩ አይችሉም።

እንዲሁም፣ ምርትዎትን መጀመር የሚፈልጉበት ገበያ ውስጥ በሰፊው ጥቅም ላይ የሚውሉትን የፍለጋ ፕሮግራሞች እና የመተግበሪያዎች መደብር ለይተው ማወቅ አይርሱ። ቻይና ውስጥ፣ Baidu በሰፊው ጥቅም ላይ ይውላል። ሩሲያ ውስጥ፣ Yandex ተመራጭ ነው። በቻይና ተጨማሪ በመቶዎች የሚቆጠሩ የተለያዩ የመተግበሪያዎች መደብሮች ሲኖሩ Google Play ግን ጥቅም ላይ እየዋለ አይደለም። ስትራቴጂዎን ትክክለኛ ባልሆኑ መንገዶች የሚያዘጋጁ ከሆነ የሶፍትዌር ሎካላይዜሽን ፕሮጀክትዎት ጎልቶ ሊታይ አይችልም። ወይም ደግሞ፣ የገበያውን ሕጎች ባለማክበርዎት ከገበያው ሊወጡ ይችላሉ።

ሎካላይዜሽን እና የቋንቋ ሙከራ

በሶፍትዌር ሎካላይዜሽን ስትራቴጂ ውስጥ መቅረት የሌለበት አንዱ ወሳኝ ደረጃ የሎካላይዜሽን እና የቋንቋ ሙከራ ነው። መልእክቱ ትርጉም እንደሚሰጥ ለማረጋገጥ ቋንቋው የሚነገርበት አካባቢ ሰዎች እንዲያረጋግጡት ያድርጉ። ሙከራውን የሚያደርጉት ሰዎች ትክክለኛዎቹን የቃላት ፍቺዎች መጠቀምዎትን እና ጽሑፉ ፍሰቱን የጠበቀ እና ለተጠቃሚዎች ማራኪ መሆኑን ያረጋግጣሉ።  የተጠቃሚ  ተሞክሮዎችን በተለያዩ ሥርዓተ ክወናዎች እና መድረኮች ላይ ተመሳሳይ ማድረግ የሚችሉ ብቁ ፕሮግራመሮችን ያሠሩ። የሎካላይዜሽን ሙከራ ሶፍትዌርዎት በአግባቡ እና በሚፈለገው ፍጥነት እንደሚሠራ ያረጋግጣል። የተቋረጡ ትርጉሞች፣ ቅርጸቶች ወይም ኮዶኮች አለመኖራቸውን ያረጋግጣል። እንዲሁም የተጠቀሟቸው ምስሎች፣ ምልክቶች፣ እና አዶዎች ከባህል አንጻር ተገቢ መሆናቸውን ደግመው ያረጋግጣሉ። እርስዎ ምርትዎትግ ላይ ስህተት ባያገኙበትም፣ ደንበኞችዎት ሊያገኙበት ይችላሉ። ከደንበኞች ቅሬታ ወይም መጥፎ አስተያየቶች ከመቀበል ይልቅ ምርትዎት የሚለቀቅበትን ጊዜ ለጥቂት ቀናት ማዘግየቱ የተሻለ አማራጭ ነው።

የመጨረሻው ውጤት

የንግድ ሥራ ሎካላይዜሽን ተገቢ የሆኑ ሂደቶች እና ኀላፊነቶች መዘጋጀት ስለሚኖርባቸው ለአንዳንዶች ይህ ሥራ እንደሚወራው መተግበሩ ቀላል እንዳልሆነ እውነት ቢሆንም፣ ይህ ማለት ግን ሎካላይዜሽን እጅግ ከባድ የሆነ ውጣ ውረድ ነው ማለት አይደለም። የሶፍትዌርዎትን፣ ድር ጣቢያዎትን ወይም የመተግበሪያዎትን ይዘት በአግባቡ ሎካላይዝ በማደረግ፣ ሎካልይዝ የሚደረግበትን ቅልጥፍና በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመር ይዘትዎትን ለገበያ የሚያቀርቡበትን ጊዜ ማፋጠን ይችላሉ። ትክክለኛዎቹን ማቀናበሪያዎች መጠቀም እና የሎካልይዜሽን ሂደቱን ማፋጠን አላስፈላጊ፣ ተደጋጋሚ በእጅ የሚሠሩ ሥራዎችን እና አስተዳደራዊ ወጪዎችን ሊያስቀር ይችላል በመሆኑም ችላ ሊባል የማይገባው ጉዳይ ነው።

የንግድ ሥራዎትን ሎካላይዝ የማድረጉን ሥራ አነስ አነስ ወዳሉ ተግባር ላይ ሊውሉ የሚችሉ ክፍሎች ይከፋፍሉት። ለዕቅድ እና ምርምር ደረጃው በቂ ጊዜ እና ሃብት መስጠትዎትን ያረጋግጡ። በቅንጅት የሚሠራ ቡድን ያዋቅሩ እንዲሁም ትክክለኛውን የትርጉም አስተዳደር ማቀናበሪያ መጠቀምዎን ያረጋግጡ። ሶፍትዌርዎትን ከጅምሩ ዓለም አቀፋዊ ያድርጉ እንዲሁም ቀደም ብለው ASO/SEOዎት ላይ በደንም ይሥሩ። እነዚህን ነገሮች ካጠናቀቁ በኋላ፣ ደጋግመው ይሞክሩት!

Leave a Reply