ወደ መላው ዓለም ንግድዎን ያስፋፉት! ለዚህ ግን ሎካላይዜሽን አስፈላጊ የሚሆንባቸው ፱ (ዘጠኝ) ዐበይት ምክንያቶች

You are currently viewing ወደ መላው ዓለም ንግድዎን ያስፋፉት! ለዚህ ግን ሎካላይዜሽን አስፈላጊ የሚሆንባቸው ፱ (ዘጠኝ) ዐበይት ምክንያቶች
ንግድ ሎካላይዜሽን

«ሎካላይዜሽን» ብሎ ነገር ደግሞ ምንድን ነው? «ከኔ ሥራስ ጋር ምን ያገናኘዋል?» ብለው ራስዎን ጠይቀዋል። ጠይቀው ከሆነ፣ ብዙ አያስቡ! ምንነቱን ከነጠቀሜታው እኛው ራሳችን እንነግርዎታለን። ሎካላይዜሽን አንድን በአንድ አገር በቴክኖሎጂ ተደግፎ የተመረተ ወይም የተዘጋጀ ምርት ወይም አገልግሎት ዒላማ በተደረገው አገር ቋንቋና ባህል በሚመጥንና በሚስማማ መልኩ አጣጥሞ ተርጒሞ በማቅረብ ዋንኛ ግቡ ገበያን ማስፋፋት የሆነ የትርጒም ሥራ ዓይነት ነው። «ሎካላይዜሽን» የሚለው ከእንግሊዝኛ የተወረሰ ቃል ለደንበኞች የሚዘጋጁ መልእክቶችን መተርጐም፣ ምስሎችን ከሚፈለገው አካባቢ ጋር እንዲመሳሰሉ ማድረግ፣ እንዲሁም የሚያቀርቧቸው ምርትና አገልግሎቴን ግዙኝ ማትጊያ ሆነ ማበረታቻ ሽልማቶችን እንዲሁም አማራጮችን የአካባቢው ሰው በሚፈልገውና በሚመቸው መልኩ ማዘጋጀትን ሥራዎች በሙሉ በአንድ ላይ የሚይዝ ፅንሰ ሐሳብ ነው።

«ሎካላይዜሽን ለኔ ምን ፋይዳ አለው?» ብለው ራስዎን ከጠየቁ ለዚህ ጥያቄዎ ያዘጋጀናቸው ፱ (ዘጠኝ) ዐበይት ምክንያቶች እነሆ በረከት፦

 ሎካላይዜሽንን በመጠቀም ቁጥሩ መጠነ ሰፊ የሆነ ታዳሚን ማግኘት ይችላሉ፦ ማስተላለፍ የሚፈልጉትን መልእክት በተለያዩ ቋንቋዎች እንዲተረጐምልዎት ሲያደርጉ፣ አዳዲስ ገበያዎችን መፍጠርና የደንበኞችዎን ብዛት ማባዛት ይችላሉ።

ሎካላይዜሽን የእርስዎን ተገልጋዮች ተመክሮ የተሻለ እንዲሆን ይደርግላቸዋል፦ ምርትዎን ወይም አገልግሎትዎን በሎካላይዜሽን ዘዴ ሲያስተረጒሙ ደንበኞች ምርትዎንና አገልግሎትዎን እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው በቀላሉ ይገባችዋል፤ በዚህም የሚኖራቸው ተመክሮ የተሻለ ብሎም የላቀ እንዲሆን ያደርግላቸዋል።

ሎካላይዜሽን ታዳሚዎችዎ ከእርስዎ ጋር የበለጠ እንዲቀራረቡ ያደርጋቸዋል፦ ደንበኞችን ወደ ምርትና አገልግሎቶችዎ ለመሳብ ከፈለጉ በቋንቋቸው ካቀረቡላቸው ወደ እርስዎ የመሳብ ዕድላቸው ከፍተኛ መሆኑ በበርካታ ጥናቶች የተረጋገጠ ነው።

ሎካላይዜሽን ደንበኞችዎን የምርትና አገልግሎትዎ ታማኝ ደንበኛ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፦ ለባህላቸውና ቋንቋቸው ዋጋ እንደሚሰጡ ለማሳየት ምርትና አገልግሎትዎን በቋንቋቸው ያቅርቡላቸው! በቋንቋቸው ያናግሯቸው! ለምርትና አገልግሎትዎ ታማኝ ደንበኞች ይሆናሉ።

በሎካላይዜሽን ተጠቅመው ሽያጭዎን ያጧጥፉ፦ ምርትና አገልግሎቶችዎን ደንበኞች እንዲረዷቸውና እንዲገዙልዎት ሁኔታዎችን ቀላል በማድረግ ሽያጭና ገቢዎን በከፍተኛ ደረጃ እንዲጨምሩልዎት ማድረግ ይችላሉ።

ሎካላይዜሽን በበይነ መረብ የፍለጋ ቅደም ተከተል ደረጃ ምርትና አገልግሎትዎን ከፊት ተሰላፊ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፦ በአገርኛ ቋንቋ የቀረበ «ማስታወቂያና ምርትና አገልግሎቴን እወቁልኝ» ጥሪ በማስተላለፍ፣ በበየነ መረብ ፍለጋ ደረጃ አሰጣጥ ግንባር ቀደም ተሳላፊ መሆን እና ደንበኞችም እርስዎን በቀላሉ እንዲያገኝዎት ማድረግ ይችላሉ።

ሎካላይዜሽንን ተጠቅመው ለደንበኞች የሚሰጡትን የድጋፍ አገልግሎት የላቀ ደረጃ ላይ ያድርሱት፦ ለደንበኞች የሚሰጡትን የድጋፍ አገልግሎት በቋንቋቸው እንዲሆንላቸው በማስደረግ፣ ደንበኞች በምርትና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚኖራቸውን የእርካታ ደረጃ ማሻሻል ይችላሉ።

ሎካላይዜሽንን መጠቀም የሰዎችን ባህልና ማንነት ግንዛቤ የላቀ እንዲሆን ያደርጋል፦ በአገርኛ ቋንቋ የቀረበ «ማስታወቂያና ምርትና አገልግሎቴን እወቁልኝ» ጥሪ በማስተላለፍ፣ ደንበኞች የበለጠ እንዲረዷቸውና በዚህም ቀና አመለካከት እንዲኖራቸው ማድረግ ይችላሉ።

ሎካላይዜሽንን በመጠቀም የሥራ ውጤታማነትዎን ይጨምሩ፦  በአገርኛ ቋንቋ የቀረበ «ማስታወቂያና ምርትና አገልግሎቴን እወቁልኝ» ጥሪ በማስተላለፍ፣ አንድን የማስታወቂያ ይዘት ለመፍጠርና ለማስተላለፍ ይፈጁ የነበረውን ጊዜና ጉልበት መቆጠብ ይችላሉ።

ለማጠቃለል ያህል፣ ሎካላይዜሽን የንግድ ሥራዎ እንዲያድግና በአዳዲስ ገበያዎች ውስጥ ስኬታማ እንዲሆን የሚያደርግ ኃይለኛ መሣሪያ ነው። መጠነ ሰፊ የሆነ ታዳሚን በአንድ ጊዜ በመድረስ፣ የተገልጋዮችዎን ተመክሮ የተሻለ እንዲሆን በማድረግ፣ ታማኝ ደንበኞችን በማፍራት፣ እና ሌሎች ተጨማሪ ጥቅሞችን በማስገኘት የንግድ ሥራዎን ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ ያደጋል። እና ታዲያ ምን እየጠበቁ ነው? የምርትና አገልግሎትዎን ሎካላይዜሽን ሥራ እንድንሠራልዎት ለኛ ዕድሉን ይስጡና ተዓምሩን አብረን እንመልከት!

Leave a Reply