Read more about the article ወደ መላው ዓለም ንግድዎን ያስፋፉት! ለዚህ ግን ሎካላይዜሽን አስፈላጊ የሚሆንባቸው ፱ (ዘጠኝ) ዐበይት ምክንያቶች
ንግድ ሎካላይዜሽን

ወደ መላው ዓለም ንግድዎን ያስፋፉት! ለዚህ ግን ሎካላይዜሽን አስፈላጊ የሚሆንባቸው ፱ (ዘጠኝ) ዐበይት ምክንያቶች

«ሎካላይዜሽን» ብሎ ነገር ደግሞ ምንድን ነው? «ከኔ ሥራስ ጋር ምን ያገናኘዋል?» ብለው ራስዎን ጠይቀዋል። ጠይቀው ከሆነ፣ ብዙ አያስቡ! ምንነቱን ከነጠቀሜታው እኛው ራሳችን እንነግርዎታለን። ሎካላይዜሽን አንድን በአንድ አገር በቴክኖሎጂ ተደግፎ የተመረተ…

Continue Readingወደ መላው ዓለም ንግድዎን ያስፋፉት! ለዚህ ግን ሎካላይዜሽን አስፈላጊ የሚሆንባቸው ፱ (ዘጠኝ) ዐበይት ምክንያቶች

«As a Man Thinketh» የሚለው መጽሐፍ 5 ዋንኛ ሐሳቦች

ትርጒም በአብዱልአዚዝ ኑርአዲስ (ኢትዮስታር ተርጓሚ) የምትሆነው ወይም የሚያጋጥምህ የምታስበውን ነው! አሁን ያለህበት ሁኔታ ሊሆን የቻለበት ምክንያት በአንድ ወቅት በነበረህ ወይም አሁንም እያሰብካቸው ባሉ ሐሳቦች ምክንያት የተፈጠረ ሁኔታ ነው። እራስህን መቀየር ከፈለግክ፣ ሐሳቦችህን በመጀመሪያ መቀየር አለብህ። እያንዳንዷ የሰው ልጅ የሚወስዳት እርምጃ መነሻዋ በድብቅ አእምሮ ውስጥ ያሉ ሐሳቦች የዘሯት ዘር ፍሬ ነች። ትክክለኛውን ሐሳብ በመምረጥና ተግባር ላይ በማዋል የሰው ልጅ ወደ ፍጹም መለኮታዊ ደረጃ ሊያድግ ይችላል። የተሳሳተ ሐሳብን ምርጫው ካደረገና ይህንኑ በተግባር ላይ ካዋለው ደረጃው ከአውሬ በታች ሊወርድ ይችላል። መልካምና ቀና ሐሳቦች በጭራሽ መጥፎ ውጤቶችን ሊያስከትሉ አይችሉም፤ መጥፎ ሐሳቦች እና ተግባሮች ፈጽሞ ጥሩ ውጤትን ሊያስገኙ አይችሉም።  አእምሮህ እንደ ዐፀደ አታክልት ነው! የመጽሐፉ ደራሲ አእምሯችንን በዐፀድነት (በቅጽረ አታክልትነት) ይመስሉታል። አእምሯችንን ማበልጸግ ወይም መረን እንዲወጣ መልቀቅ የኛው የራሳችን ምርጫ ነው። በአታክልት ቦታችን ላይ ውብ የአበባ ዘሮችን ካልተከልን ስፍራው በራሱ ያልተፈለጉ አረሞችን ማብቀል ይጀምራል። ልክ አትክልተኛው አላስፈላጊ ተክሎችን (አረሞችን) መንጥሮ እንደሚያስወግዳቸው ሁሉ እያንዳንዱ ግለሰብም ትክክለኛዎቹን የሐሳብ ዘሮች በአእምሮው ውስጥ መትከል፣ መንከባከብና አረሞች ሲከሰቱ ሙሉ በሙሉ እየመነጠረ የማጥፋት ኃላፊነት አለበት። ይህን ስናደርግ ሕይወታችን ውብ እንደሆነ ይቀጥላል። ተቃራኒውን ስናደርግ ደግሞ አረሞቹን ለመመገብ ስለምንገደድ ሕይወታችን ይቃወሳል። ሐሳቦች በአእምሮ ላይ ብቻ ሳይሆን በአካል ላይም ተፅዕኖ ያሳርፋሉ! እንዴት እንደምናስብ እና ምን እንደምናስብ በአእምሮ ላይ ብቻ ሳይሆን በአካላችንም ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያሳርፋል። ሰውነታችን የአእምሯችን ባሪያ ነው። ስለሆነም ታስቦበትም ሆነ ሳይታሰብበት የታሰበ ነገር በቀጥታ ለሰውነታችን ሲደርሰው ሰውነታችን ትዕዛዙን ሳያወላውል  አክብሮ ተፈጻሚ ያደርጋል። የመድሐፉ ደራሲ በቀጣይነት በበሽታ የመያዝ ስጋት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ዞሮ ዞሮ በበሽታው እንደሚያዙ ይናገራሉ። ስለዚህ ጤናማ  መሆን ማለት ሰውነትን ብቻ ሳይሆን የአእምሮ ጤናማነትን በይበልጥ የሚመለከት ጉዳይ ነው። ሐሳቡን መለወጥ ያልቻለ ሰው አመጋገቡን ቢለውጥ ለሰውነቱ ምንም እርባና አይኖረውም። በተመሳሳይ መልኩ በአእምሯችን የሚመላለሱ ሐሳቦች እርጅናን ሊያስከትሉ ይችላሉ። ትንሽ ጊዜ ትኩረት ሰጥተን በዙሪያችን ያሉ ሰዎችን ብንታዘባቸው ፊታቸው በፈገግታ የተሞላ ዕድሜያቸው በዘጠናዎቹ ውስጥ ያሉ አዛውንቶችን እናያለን። በተቃራኒው ገና ዕድሜያቸው  በሠላሳዎቹ አጋማሽ ውስጥ ያሉ ፊታቸው በእርጅና መሥመሮች የተሸበሸበ ያለጊዜያቸው ያረጁ ጎልማሶችንም በዚያው ልክ እናያለን። ማንነትህ በዙሪያህ ባሉ ሁኔታዎች የሚወሰን አይደለም! አንድ ነገር ማግኘት ፈልገህ የማታገኘው የመጣህበት የሕይወት ጎዳና ከሌሎች የተለየ ስለሆነ ወይም ያለህበት አካባቢ አንተን ስለማይፈልግህ ወይም ስላልተቀበለህ መስሎ ከተሰማህ፣ ወዳጄ ሆይ ልብ በል ክፉኛ ስተሃል። ማንነትህ በዙሪያህ ባሉ ሁኔታዎች የሚወሰን አይደለም።  እንዲያውም ከአእምሮህ ውጭ ያለው ዓለም በአንተ ሐሳቦች የሚንሸራሸርበት ውስጣዊው ዓለምህ ይዘወራል እንጂ አይዘወርም። በዙሪያህ ያሉት ሁኔታዎች ምንም ይሁኑ ምን ሁልጊዜም አፀፋ ምላሽ የምትሰጥበትን መንገድ መምረጥ ምርጫው ያንተ ነው። የመምረጥ ሙሉ ነጻነት አለህ። በመሆኑም በቁጥጥርህ ሥር የሆኑት ነገሮች ላይ ትኩረት ማድረግ የተሻለው አፀፋ ምላሽ መስጫ አማራጭ መንገድህ  ነው። መቆጣጠር በምትችላቸው ነገሮች ላይ ስታተኩርና በእነርሱ ላይ መሻሻሎችን ስታደርግ በሕይወት ትግል ውስጥ አሸናፊ እየሆንክ ወደፊት ትቀጥላለህ። ብዙ ሰዎች በዙሪያቸው ያሉ ሁኔታዎችን ለመቀየር ይጨነቃሉ። ይሁን እንጂን ራሳቸውን ለመቀየር ግን ፍጹም ፈቃደኛ አይደሉም። በመሆኑም ዕድሜ ልካቸው በአስጨናቂ መፍትሔ አልባ ሐሳቦቻቸው እንደታሰሩ ሰርክ ይኖራሉ። የምታወስዳቸው እርምጃዎችና ሐሳቦችህ አንድ ላይ በስምረት መጓዝ አለባቸው! አንዳንድ የማኅበረሰብ አንቂ ነን የሚሉ ሰዎች የሚሰብኩት ስብከት ያመንከበት ሐሳብ ሁሉ ወደ ስኬታማነት ይቀየራል የሚል ድምዳሜን ይሰጣል። ይህ አባባል ከስበት ሕግ ጋር እንዲቆራኝ ስለተደረገም ሐሳቡ ለብዙ ሰዎች ይቸበቸብላቸዋል። የአነቃቂ ንግግሮችና ፍልሰፍና አብዮት ፈር ቀዳጅ አብዮተኛ የሆነው ማኅበረሰብ አንቂ ጄምስ አለን የሐሳብ በአእምሮ ውስጥ መኖር ብቻ  በቂ እንዳልሆነ በግልጽ ተናግሯል። ሐሳብ መነሻ ነጥብ ብቻ ናቸው። ስለሆነም ሐሳባችንን ከትክክለኛው መወሰድ ያለበት እርምጃዎ ጋር እንዲጣመር ካላደረግን ያቀድነውን ነገር መቼም ቢሆን አናሳካም። ነገሮች እንዲሆኑልህ መመኘት እና ወደ አንተ እስኪመጡ ድረስ መጠበቅ በምንም ዓይነት መንገድ ላንተ የሚሰጥህ ፋይዳ አይኖረውም። ማንኛውንም የምትፈልገውን ነገር ለማግኘት ወደፊት መጓዝ፣ ትክክለኛውን እርምጃ መውሰድ እና አስፈላጊውን ጥረት ሁሉ ማድረግ  ይኖርብሃል።

Continue Reading«As a Man Thinketh» የሚለው መጽሐፍ 5 ዋንኛ ሐሳቦች

በጀምስ ክሊር የተጻፈው “Atomic Habits” (ጥቃቅን ግን ወሳኝ ልማዶች) ከሚለው መጽሐፍ  የተወሰዱ 10 አንኳር ቁምነገሮች

1. ልማድ ምን ማለት ነው? ልማድ ማለት ብዙውን ጊዜ በነሲብ በተደጋጋሚ የሚፈጸም ድርጊት ነው። መጀመሪያ ላይ እንዲሁ ሲታዩ ቀላልና እዚህ ግቡ የማይባሉ ለውጦች በጊዜ ሂደት አስደማሚ ልዩነትን ይፈጥራሉ። 2. እንዴት…

Continue Readingበጀምስ ክሊር የተጻፈው “Atomic Habits” (ጥቃቅን ግን ወሳኝ ልማዶች) ከሚለው መጽሐፍ  የተወሰዱ 10 አንኳር ቁምነገሮች

ከመፃህፍት የተገኘ ፥ ለጊዜ ተዋቸው!

ከመፃህፍት የተገኘለጊዜ ተዋቸው!በአንድ ትንሽ መንደር ውስጥ የሚኖር አንድ ሰው ነበር። ታዲያ ይህ ሰው፣ በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ በኑሮው ከሚገጥመው ችግር የተነሳ፣ ሁልጊዜም በህይወቱ ደስተኛ አልነበረም። አንድ ቀን ግን ከሚኖርበት ሥፍራ…

Continue Readingከመፃህፍት የተገኘ ፥ ለጊዜ ተዋቸው!

ሁሉም_ነገር_ለበጎ_ነው

አንድ ንጉስ ከአሽከሩ ጋር ለአደን ወደ ጫካ ያመራል። ዙርያውን ወጥመድ በማጥመድ ላይ ሳሉ አንደኛው ወጥመድ የንጉሱን እጅ ላይ አርፎ እጁን ያሳጠዋል። ንጉሱም በመጮህ ላይ ሳለ አሽከሩ የደማውን እጁን በጨርቅ እየጠቀለለ…

Continue Readingሁሉም_ነገር_ለበጎ_ነው

በራስ መተማመን እንዴት እንገነባለን ???

ለአንድ ግለሰብ ከሚያስፈልጉት መሠረታዊ የስነ-ልቦና እሴቶች መካከል አንዱና ዋነኛው በራስ መተማመን (self confidence) ነው፡፡ ብዙዎቻችን በራስ መተማመናችን አነስተኛ ወይም ከነጭራሹ ባለመኖሩ ምክንያት ያጣናቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ ለመሆኑ በራስ መተማመን ምንድን…

Continue Readingበራስ መተማመን እንዴት እንገነባለን ???

ሞክሼ ፊደላት

ሞክሼ ፊደላት የሚባሉት አንድ ዓይነት ድምፅ ያላቸው ነገር ግን በቅርጽ እና በሥራቸው የተለያዩ ፊደላት የሆኑ ናቸው። በድሮ ጊዜ ግን አባቶቻችን ሀን ከ ሐ ፣ ጸን ከ ፀ… ፊደሎችን በድምፅ አወጣጥ…

Continue Readingሞክሼ ፊደላት

ሎካላይዝ የሚደረገውን ሶፍትዌር ማዘጋጀት – ክፍል 3

ሎካላይዜሽን ጠቃሚ ያልሆነ እና ብዙ ጊዜ የሚፈጅ ነገር ተደርጎ ይወሰዳል፣ በዚህም ምክንያት ብዙ ድርጅቶች ጊዜው እስኪረፍድ ድረስ ለጉዳዩ ቦታ አይሰጡትም። ሶፍትዌር አዘጋጆቹ ኮዱን ሲያዘጋጁ ለሌሎች ቋንቋዎች፣ ዓለም አቀፋዊ ቅርጾች ወይም…

Continue Readingሎካላይዝ የሚደረገውን ሶፍትዌር ማዘጋጀት – ክፍል 3

የሎካላይዜሽን ሥራ እንዴት መጀመር ይቻላል? ክፍል 2

በአብዛኛው፣ ሶፍትዌርዎትን ወይም ድር ጣቢያዎን ሎካላይዝ ለማድረግ የሚያወጡት አጠቃላይ ወጪ፣ ሥራው ከሚፈጥራቸው ዕድሎች ከሚገኘው ተመላሽ ያነሰ ነው የሚሆነው። ምርትዎትን ወይም አገልግሎትዎትን ሎካላይዝ ለማድረግ ከወሰኑ፣ ምርቱ ወይም አገልግሎቱ ሎካላይዝ ለመደረግ ዝግጁ…

Continue Readingየሎካላይዜሽን ሥራ እንዴት መጀመር ይቻላል? ክፍል 2

ሎካላይዜሽን ለንግድ ሥራ አስፈላጊነቱ ምንድነው? ክፍል 1

1- ሎካላይዜሽን ለንግድ ሥራ አስፈላጊነቱ ምንድነው? የንግድ ሥራ ሲሠራ ሁሌም ቢሆን ወጪዎች ይኖራሉ፣ ሆኖም ግን ከልክ በላይ መሆን የለበትም። ብዙ ድርጅቶች ምርቶቻቸውን ሎክላይዝ ማድረግ ተጨማሪ የአስተዳደር ወጪዎችን የሚያስከትል እና ምርቱ…

Continue Readingሎካላይዜሽን ለንግድ ሥራ አስፈላጊነቱ ምንድነው? ክፍል 1

ጥራቱን የጠበቀ የትርጒም አገልግሎት

ጥራቱን የጠበቀ የትርጒም አገልግሎት ማግኘት ይፈልጋሉ? በተመጣጣኝ ዋጋ ከ20 በሚበልጡ ቋንቋዎች መተርጎም እንችላለን። በቀጥታ በበይነ መረብ በፍጥነት አገልግሎት እንሰጣለን። ከ50 በላይ የሆኑ በሙያው የሠለጠኑ ተርጓሚዎቻችን አብዛኛዎቹን የኢትዮጵያና ምሥራቅ አፍሪካ ቋንቋዎች…

Continue Readingጥራቱን የጠበቀ የትርጒም አገልግሎት

End of content

No more pages to load