በትርጒም ፕሮጄክቶች ላይ ተባብሮ የመሥራት አስፈላጊነት
መግቢያ ወደ አንድ መንደርነት እየተቀየረች ባለችው በርካታ ቋንቋዎች የሚነገሩባት ዓለማችን የትርጒም ሥራ አንዱና ዋንኛው የተግባቦት መሣሪያ ነው። ከአንዱ ቋንቋ ወደ ሌላው የጽሑፍ መልእክት በሚተላለፍበት ወቅት የሚፈለገውን ውጤት ማግኘት እንዲቻል ከፍተኛ…
መግቢያ ወደ አንድ መንደርነት እየተቀየረች ባለችው በርካታ ቋንቋዎች የሚነገሩባት ዓለማችን የትርጒም ሥራ አንዱና ዋንኛው የተግባቦት መሣሪያ ነው። ከአንዱ ቋንቋ ወደ ሌላው የጽሑፍ መልእክት በሚተላለፍበት ወቅት የሚፈለገውን ውጤት ማግኘት እንዲቻል ከፍተኛ…
«ሎካላይዜሽን» ብሎ ነገር ደግሞ ምንድን ነው? «ከኔ ሥራስ ጋር ምን ያገናኘዋል?» ብለው ራስዎን ጠይቀዋል። ጠይቀው ከሆነ፣ ብዙ አያስቡ! ምንነቱን ከነጠቀሜታው እኛው ራሳችን እንነግርዎታለን። ሎካላይዜሽን አንድን በአንድ አገር በቴክኖሎጂ ተደግፎ የተመረተ…
ውድ የኢትዮስታር ተከታታዮች፣ ከሰሞኑ ብዙ የራስ ማጥፋቶችና የድባቴ ዜናዎች መብዛታቸውን አስተውላችሁ ይሆናል። እስኪ ዛሬ ወገናችንን እያሳጣን ስላለው እና እንደ ወረርሽኝ እየተንሰራፋ ስላለው ድባቴ (ዲፕረሽን) እንወያይ። የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚገልጸው ድባቴ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአካል ጉዳተኝነት ዋነኛ መንስኤ ነው። በአለም አቀፍ ደረጃ በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ከ300 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በዚህ በሽታ ይሠቃያሉ። የበሽታው መከሰት በሁሉም ቦታ እየጨመረም ይገኛል። ዲፕረሽን እንደ መንስኤ ወይም ውጤት በመሆን የበሽታ መከላከያዎችን ጨምሮ ብዙ የሰውነት ስርዓቶችን የሚያጠቃ ውስብስብ የስነ-ልቦና እክል ነው። የእንቅልፍ መረበሽ እና የምግብ ፍላጎት ውስጥ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል። በአንዳንድ ሁኔታዎች ክብደት መቀነስ ያስከትላል፣ በሌሎች ውስጥ ለክብደት መጨመር አስተዋጽኦ ያደርጋል። ዲፕረሽን ብዙውን ጊዜ ከጭንቀት ጋር አብሮ ይመጣል። ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በአብዛኛው ሁለቱ ሁኔታዎች አብረው መከሰታቸው ነው። ምልክቶቹ *** ዲፕረሽን ያለባቸው ሁሉም ሰዎች ሁሉንም ምልክቶች ላያሳዩ ይችላሉ። አንዳንዶች ጥቂት ብቻ አንዳንዶች ደግሞ ብዙ የዲፕረሽን ምልክቶችን ሊያሳዩ ይችላሉ። የህመሙ ምልክት ከግለሰብ ግለሰብ እና በጊዜ ሂደት ይለያያል። ዲፕረሽን ብዙውን ጊዜ የማያቋርጥ ሀዘን፣ ጭንቀት ወይም ባዶ ስሜትን ያካትታል። የተስፋ መቁረጥ ወይም የተስፋ ማጣት ስሜት እና የጥፋተኝነት ስሜት፣ ዋጋ ቢስነት ወይም አቅመ ቢስነት እንዲሁም የግብረ ሥጋ ግንኙነትን ጨምሮ በትርፍ ጊዜ ማሳለፊያዎች እና እንቅስቃሴዎች ላይ ፍላጎት ወይም ደስታን ማጣትን ሊያካትት ይችላል። የኃይል መቀነስ፣ የድካም ስሜት ወይም «የዘገየ» ስሜት እንዲሁም እረፍት ማጣት፣ መበሳጨት እና ትኩረትን መሰብሰብ፣ ማስታወስ ወይም ውሳኔ ማድረግ መቸገር የተለመደ ነው። የመንፈስ ጭንቀት ያለባቸው ብዙዎች ስለ ሞት ወይም ራስን ስለ ማጥፋት ያስባሉ። የመንፈስ ጭንቀት ያለባቸው ሰዎች በእንቅልፍ (እንቅልፍ ማጣት፣ በጠዋት መነቃቃት ማጣት ወይም ከመጠን በላይ መተኛት) እና በአመጋገብ ባህሪ (የምግብ ፍላጎት ለውጥ፣ ክብደት መቀነስ ወይም መጨመር) ላይ መስተጓጎል ሊያጋጥማቸው ይችላል። የማያቋርጡ አካላዊ ምልክቶች ደግሞ ራስ ምታት፣ የምግብ መፈጨት ችግር እና ሥር የሰደደ ሕመምን ሊያካትቱ ይችላሉ። የድባቴ (ዲፕረሽን) ምክንያቶች *** ድባቴ ውስብስብ በሽታ ነው። በትክክል መንስኤው ምን እንደሆነ ማንም አያውቅም። ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል። አንዳንድ ሰዎች በከባድ የሕክምና ሕመም ወቅት ድባቴ ያጋጥማቸዋል፣ ሌሎች እንደ መንቀሳቀስ አለመቻል ወይም የሚወዱትን ሰው በሞት ማጣት በመሳሰሉ የህይወት ለውጦች ድባቴ ሊያጋጥማቸው ይችላል። ሌሎች ደግሞ በዘር የሚመጣ ድባቴ ይኖርባቸዋል እናም ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በሀዘን እና በብቸኝነት ሊዋጡ ይችላሉ። የሚከተሉትን ጨምሮ ብዙ ነገሮች በድባቴ የመጠቃት እድልን ይጨምራሉ፤ ጥቃት፦ አካላዊ፣ ወሲባዊ ወይም ስሜታዊ ጥቃት በኋለኛው ህይወትዎ ለድባቴ የበለጠ ተጋላጭ ያደርግዎታል። ዕድሜ፦ በዕድሜ የገፉ ሰዎች ለድባቴ የተጋለጡ ናቸው። እንደ ብቻውን መኖር እና የማህበራዊ ድጋፍ እጦት ባሉ ሌሎች ሁኔታዎች ይበልጥ ሊባባስ ይችላል። አንዳንድ መድኃኒቶች፦ እንደ አይዞሬቲኖይን (ብጉርን ለማከም ጥቅም ላይ የሚውለው)፣ ፀረ ቫይረስ መድኃኒት ኢንተርፌሮን-አልፋ እና ኮርቲሲቶይድ ያሉ አንዳንድ መድኃኒቶች ድባቴን ይጨምራሉ። ግጭት፦ ባዮሎጂያዊ ተጋላጭነት ባለው ሰው ላይ የሚኖር ድባቴ በግላዊ ግጭቶች ወይም ከቤተሰብ አባላት ወይም ጓደኞች ጋር ባለ ያለመግባባት ሊከሰት ይችላል።…
አብዛኛዎቻችን እንደምናውቀው በዐቢይ ጾም ከሰርክ ሆሳዕና ጀምሮ እስከ ትንሣዔ ሌሊት ያሉት ዕለታት የሚገኙበት ሳምንት ሰሙነ ሕማማት በመባል ይታወቃል። እነዚህ በሰሙነ ሕማማት ውስጥ ያሉት ቀናት የዓመተ ፍዳ እና የዓመተ ኩነኔ መታሰቢያ ናቸው።ታዲያ በእነዚህ ቀናት የተለያዩ ትውፊታዊና ሃይማኖታዊ ክንዋኔዎች ይደረጋሉ። ከነዚህ ክንዋኖዎች ውስጥ ፮ቱን ዋንኛ የሰሙነ ሕማማት ሃይማኖታዊ ትውፊታዊ ክንዋኔዎች አለመሳሳም፣ አክፍሎት፣ ቄጤማ ማሰር፣ ጥብጠባ፣ ጉልባን እና ሕፅበተ እግር በዛሬው ቀን ጸሎተ ሐሙስ እየተባለ በሚጠራውና ጉልባን በሚበላበት ዕለት…
መግቢያ የመሪነት ጥበብ ብዙ ሰዎች እንዲኖራቸው የሚመኙት እጅግ አስፈላጊ ችሎታ ነው። የመሪነት ጥበብ ስንል አንድን የጋራ ግብ ለመምታት እንዲቻል ሌሎችን ከጎን በማሰለፍ በአንድ ልብ እኩል እንዲተጉ ልባቸውን የማሸነፍ ችሎታ ማለታችን…
በ Esteban Ortiz-Ospina እና Diana Beltekian ትርጒም በብሩክ በየነ ኦርጂናሌው ጽሑፍ በእንግሊዝኛ ኦገስት 14/ 2018 ተጻፈ ወደ ዐማርኛ መጋቢት 2 ቀን 2015 ዓ.ም. ተተረጐመ በየትኛውም የዓለማችን ክፍል ሴቶች ከወንዶች ይልቅ ረዥም ዕድሜ እንዳላቸው ተረጋግጧል – ይሁንና ዕውነታው ሁልግዜ እንዲህ አልነበረም። ከበለጸጉ አገራት የተገኘው ውሂብ (ዳታ) ሴቶች በ19ኛው ክፍለዘመን ከወንዶች ይልቅ ዕድሜያቸው አጭር እንደነበረ ያሳያል። እንዲህ ከሆነ ታዲያ ዛሬ ምን ተገኝቶ ነው ሴቶች ከወንዶች ይልቅ የተሻለ ዕድሜ ያላቸው? በምን ምክንያት ሴቶች ዕድሜያቸው ከወንዶች ይልቅ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ ሄደ? ማቅረብ የምንችለው ማስረጃ ውስንነት አለው። ያልተሟላ ምላሽ ብቻ መስጠት ነው የምንችለው። ሆኖም ግን ምንም እንኳ እያንዳንዱ ምክንያት ምን ያክል ከባድ ተፅዕኖ እንዳለው በእርግጠኝነት መናገር ባንችልም ሴቶች ከወንዶች ይልቅ ረዥም ዘመን እንዲኖሩ ሥነ ሕይወታዊ (ባዮሎጂካል)፣ ሥነ ባሕሪያዊ እና አካባቢያዊ ሁኔታዎች የየራሳቸውን አስተውዋፅኦ እንዳደረጉ እናውቃለን። የተፅዕኖው ክብደቱ ምን ያክል መሆኑ ከግምት ሳይገባ ከቀደሞው ጊዜ ይልቅ በአሁኑ ዘመን ሴቶች ለምን ከወንዶች ይልቅ ረዥም ዕድሜ እንዳላቸው ቢያንስ በተወሰነ መልኩ በእርግጠኝነት መናገር እንችላለን። ለዚህም ሥነ ሕይወታዊ ያልሆኑ አንዳንድ ቁልፍ ምክንያቶችን መጥቀስ ይቻላል። እንግዲያው እነዚህን ቁልፍ ምክንያቶች ምን እንደሆኑ ለማየት እንሞክር። አንዳንዶቹ በቀላሉና በግልጽ የሚታዩ ናቸው። ለአብነት ወንዶች ከሴቶች ይልቅ ሲጋራ ብዙ ያጨሳሉ። ሌሎቹ ምክንያቶች ደግሞ ውስብስብ ናቸው። ለምሳሌ፣ በበለጸጉት አገራት ከአንድ ክፍለ ዘመን ሴቶችን ይበልጥ ሲያጠቁ የነበሩ በሽታዎች በሕክምናው ዘርፍ በመጣው ዕድገት ምክንያት በሽታዎቹን በቁጥጥር ሥር ማዋል ስለተቻለ የሴቶችን ረዥም ዕድሜ የመኖር ዕድል የዚያኑ ያክል በከፍተና ቁጥር እንዲያሻቅብ አድርጓል። በየትኛውም የዓለማችን ክፍል ሴቶች ከወንዶች ይልቅ ረዥም ዕድሜ ይኖራሉ ከዚህ በታች የሚታየው ቻርት ወንዶችና ሴቶች በወሊድ ወቅት ያላቸውን በሕይወት የመቆየት ዕድል ያሳያል።ለሁላችንም በግልጽ እንደሚታየው ሁሉም አገሮች አግድም ከተሠመረው አካፋይ መሥመር በላይ ናቸው – ይህ ማለት በሁሉም አገሮች ውስጥ ያሉ አዲስ የተወለዱ ሴት ጨቅላ ሕፃናት አዲስ ከተወለዱ ጨቅላ ወንድ ሕፃናት ይልቅ በሕይወት የመኖር ዕድል አላቸው። በሚገርም ሁኔታ ይኸው ቻርት ሴቶች የተሻለ ዕድል በየትኛውም አገር እንዳላቸው እያሳየ በአገራት መካከል ያለው ልዩነት ደግሞ ሰፊ ነው። ሩሲያ ውስጥ ሴቶች ከወንዶች ይልቅ 10 ዓመት የበለጠ ይኖራሉ፤ በብሁታን ደግሞ ልዩነቱ አንድ ዓመት እንኳ አይደፍንም። በበለጸጉ አገራት ሴቶች ያላቸው የተሻለ በሕይወት የመኖር ዕድል መጠኑ ያነሰ ነው አሁን ደግሞ በጊዜ ሂደት እንዴት የሴቶች በሕይወት ረዥም ዕድሜ የመቆየት ዕድል እየተሻሻለ እንደሄደ እንመልከት። ከዚህ በታች ያለው ቻርት እ.አ.አ. ከ 1790 እስከ 2014 ባለው ጊዜ ውስጥ በአሜሪካ ውስጥ የወንዶችና የሴቶች በሕይወት የመቆየት ዕድል እንዴት እንደነበረ ያመላክታል። እዚህ ላይ ሁለት ጉዳዮች ጎልተው ወጥተው ይታያሉ። በመጀመሪያ ሽቅብ ወደ ላይ የሚወጣ አዝማሚያ ይታያል፦ ሁለቱም ወንዶችና ሴቶች በአሜሪካ ውስጥ ዛሬ ላይ ከአንድ ክፍለ ዘመን በፊት ይኖሩ ከነበረው ይልቅ የተሻለ ረዥም ዕድሜ ይኖራሉ። ይህ እውነታ በመላው ዓለም ዙሪያ የሰው ልጅ ዕድሜ ላይ ከታየው ታሪካዊ መሻሻል ጋር የተጣጣመ ነው። በሁለተኛ ደረጃ፣ መጠኑ እየሰፋ የሚሄድ ክፍተት ይታይል፦ ሴቶች ረዥም ዕድሜ የመኖር ዕድላቸው በፊት ላይ በጣም አነስተኛ ነበረ ሆኖም ግን ባለፈው ክፍለ ዘመን በጉልህ በሚታይ ደረጃ መሻሻል አሳይቶ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል። በቻርቱ ላይ የተቀመጠውን ‘አገር መቀየሪያ’…
ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን በዓለም ዙሪያ ያሉትን ሴቶች ስኬት ዕውቅና እና ተገቢውን ክብር ለመስጠት የምንጠቀምበት የተለየ ቀን ነው። በያዝነው ዓመት ክብረ በዓሉን የኮምፒውተር ሳይንቲስት እና በአርቴፊሻል አስተውሎት (አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ) መስክ…
የአድዋ ጦርነት የአድዋ ጦርነት በ19ኛው ክፍለ ዘመን የአፍሪካዋ ኢትዮጵያንና የአውሮፓ ሀያልዋን ያፋጠጠ ታላቅ ታሪክ ቀያሪ ግጭት ሲሆን አፍሪካውያን የአውሮፓን ገዢ ሀይላት በድል እንደ ሀገር ብሎም እንደ አህጉር መመከት የጀመሩበት ምዕራፍ…
ከመፃህፍት የተገኘለጊዜ ተዋቸው!በአንድ ትንሽ መንደር ውስጥ የሚኖር አንድ ሰው ነበር። ታዲያ ይህ ሰው፣ በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ በኑሮው ከሚገጥመው ችግር የተነሳ፣ ሁልጊዜም በህይወቱ ደስተኛ አልነበረም። አንድ ቀን ግን ከሚኖርበት ሥፍራ…
አንድ ንጉስ ከአሽከሩ ጋር ለአደን ወደ ጫካ ያመራል። ዙርያውን ወጥመድ በማጥመድ ላይ ሳሉ አንደኛው ወጥመድ የንጉሱን እጅ ላይ አርፎ እጁን ያሳጠዋል። ንጉሱም በመጮህ ላይ ሳለ አሽከሩ የደማውን እጁን በጨርቅ እየጠቀለለ…
ለአንድ ግለሰብ ከሚያስፈልጉት መሠረታዊ የስነ-ልቦና እሴቶች መካከል አንዱና ዋነኛው በራስ መተማመን (self confidence) ነው፡፡ ብዙዎቻችን በራስ መተማመናችን አነስተኛ ወይም ከነጭራሹ ባለመኖሩ ምክንያት ያጣናቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ ለመሆኑ በራስ መተማመን ምንድን…
ክፍል አንድ ሰላም ለእናንተ ውሸትን የተለያዩ ምሁራን ትርጓሜና እና ማብራሪያ ሰጥተውበታል በዚህም ነጋሪውን ለመጥቀም የታሰበ ሐሰታዊ የሆነ ግንኙነት(ሚሼል) የሚለው መጀመሪያው ሲሆን ይህም ብዙ ውዝግቦችን አስነስቶ ነበር፡፡ምክንያቱም ነጋሪውን ብቻ ለመጥቀም ውሸት…
ሞክሼ ፊደላት የሚባሉት አንድ ዓይነት ድምፅ ያላቸው ነገር ግን በቅርጽ እና በሥራቸው የተለያዩ ፊደላት የሆኑ ናቸው። በድሮ ጊዜ ግን አባቶቻችን ሀን ከ ሐ ፣ ጸን ከ ፀ… ፊደሎችን በድምፅ አወጣጥ…
ሎካላይዜሽን ጠቃሚ ያልሆነ እና ብዙ ጊዜ የሚፈጅ ነገር ተደርጎ ይወሰዳል፣ በዚህም ምክንያት ብዙ ድርጅቶች ጊዜው እስኪረፍድ ድረስ ለጉዳዩ ቦታ አይሰጡትም። ሶፍትዌር አዘጋጆቹ ኮዱን ሲያዘጋጁ ለሌሎች ቋንቋዎች፣ ዓለም አቀፋዊ ቅርጾች ወይም…
በአብዛኛው፣ ሶፍትዌርዎትን ወይም ድር ጣቢያዎን ሎካላይዝ ለማድረግ የሚያወጡት አጠቃላይ ወጪ፣ ሥራው ከሚፈጥራቸው ዕድሎች ከሚገኘው ተመላሽ ያነሰ ነው የሚሆነው። ምርትዎትን ወይም አገልግሎትዎትን ሎካላይዝ ለማድረግ ከወሰኑ፣ ምርቱ ወይም አገልግሎቱ ሎካላይዝ ለመደረግ ዝግጁ…
1- ሎካላይዜሽን ለንግድ ሥራ አስፈላጊነቱ ምንድነው? የንግድ ሥራ ሲሠራ ሁሌም ቢሆን ወጪዎች ይኖራሉ፣ ሆኖም ግን ከልክ በላይ መሆን የለበትም። ብዙ ድርጅቶች ምርቶቻቸውን ሎክላይዝ ማድረግ ተጨማሪ የአስተዳደር ወጪዎችን የሚያስከትል እና ምርቱ…
At some point you may have wondered or asked yourself: what does the term localization really mean? If you have, don’t feel bad. Few people outside the industry can describe…
ጥራቱን የጠበቀ የትርጒም አገልግሎት ማግኘት ይፈልጋሉ? በተመጣጣኝ ዋጋ ከ30 በሚበልጡ ቋንቋዎች መተርጎም እንችላለን። በቀጥታ በበይነ መረብ በፍጥነት አገልግሎት እንሰጣለን።ከ80 በላይ የሆኑ በሙያው የሠለጠኑ ተርጓሚዎቻችን አብዛኛዎቹን የኢትዮጵያና ምሥራቅ አፍሪካ ቋንቋዎች ከአብዛኛዎቹ…
ጥራቱን የጠበቀ የትርጒም አገልግሎት ማግኘት ይፈልጋሉ? በተመጣጣኝ ዋጋ ከ20 በሚበልጡ ቋንቋዎች መተርጎም እንችላለን። በቀጥታ በበይነ መረብ በፍጥነት አገልግሎት እንሰጣለን። ከ50 በላይ የሆኑ በሙያው የሠለጠኑ ተርጓሚዎቻችን አብዛኛዎቹን የኢትዮጵያና ምሥራቅ አፍሪካ ቋንቋዎች…
Records show there are more than 1,600 businesses that are registered in Addis Ababa, Ethiopia to provide translation services. So why should you choose us, Ethiostar Translation and Localization, out…