Read more about the article በትርጒም ፕሮጄክቶች ላይ ተባብሮ የመሥራት አስፈላጊነት
ትርጒም ፕሮጄክቶች The Power of Collaboration

በትርጒም ፕሮጄክቶች ላይ ተባብሮ የመሥራት አስፈላጊነት

መግቢያ ወደ አንድ መንደርነት እየተቀየረች ባለችው በርካታ ቋንቋዎች የሚነገሩባት ዓለማችን የትርጒም ሥራ አንዱና ዋንኛው የተግባቦት መሣሪያ ነው። ከአንዱ ቋንቋ ወደ ሌላው የጽሑፍ መልእክት በሚተላለፍበት ወቅት የሚፈለገውን ውጤት ማግኘት እንዲቻል ከፍተኛ…

Continue Readingበትርጒም ፕሮጄክቶች ላይ ተባብሮ የመሥራት አስፈላጊነት
Read more about the article ወደ መላው ዓለም ንግድዎን ያስፋፉት! ለዚህ ግን ሎካላይዜሽን አስፈላጊ የሚሆንባቸው ፱ (ዘጠኝ) ዐበይት ምክንያቶች
ንግድ ሎካላይዜሽን

ወደ መላው ዓለም ንግድዎን ያስፋፉት! ለዚህ ግን ሎካላይዜሽን አስፈላጊ የሚሆንባቸው ፱ (ዘጠኝ) ዐበይት ምክንያቶች

«ሎካላይዜሽን» ብሎ ነገር ደግሞ ምንድን ነው? «ከኔ ሥራስ ጋር ምን ያገናኘዋል?» ብለው ራስዎን ጠይቀዋል። ጠይቀው ከሆነ፣ ብዙ አያስቡ! ምንነቱን ከነጠቀሜታው እኛው ራሳችን እንነግርዎታለን። ሎካላይዜሽን አንድን በአንድ አገር በቴክኖሎጂ ተደግፎ የተመረተ…

Continue Readingወደ መላው ዓለም ንግድዎን ያስፋፉት! ለዚህ ግን ሎካላይዜሽን አስፈላጊ የሚሆንባቸው ፱ (ዘጠኝ) ዐበይት ምክንያቶች
Read more about the article “12 Rules For Life“ ከሚለው በ Jordan Peterson የተጻፈው መጽሐፍ የተወሰዱ 12 አንኳር ትምህርቶች
Jordan Peterson, 12 Rules for Life

“12 Rules For Life“ ከሚለው በ Jordan Peterson የተጻፈው መጽሐፍ የተወሰዱ 12 አንኳር ትምህርቶች

ትርጒም በብሩክ በየነ 1) ወገብህን ታጠቅህ አንገትህን ቀና አድርገህ ሕይወትን ተጋፈጣት ድሃና ጭንቀትም ሰው ከሰው ቀድሞ በገፍ ይሞታል። ከበሽታ አምጪ ተሕዋሲያን ጋር ግንኙነት በሌላቸው የበሽታ ዓይነቶች ከሌሎች ይልቅ የመያዝ ዕድሉ ከፍተኛ…

Continue Reading“12 Rules For Life“ ከሚለው በ Jordan Peterson የተጻፈው መጽሐፍ የተወሰዱ 12 አንኳር ትምህርቶች
Read more about the article ድባቴ/Depression 
Depression Awareness

ድባቴ/Depression 

ውድ የኢትዮስታር ተከታታዮች፣ ከሰሞኑ ብዙ የራስ ማጥፋቶችና የድባቴ ዜናዎች መብዛታቸውን አስተውላችሁ ይሆናል። እስኪ ዛሬ ወገናችንን እያሳጣን ስላለው እና እንደ ወረርሽኝ እየተንሰራፋ ስላለው ድባቴ (ዲፕረሽን) እንወያይ።  የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚገልጸው ድባቴ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአካል ጉዳተኝነት ዋነኛ መንስኤ ነው። በአለም አቀፍ ደረጃ በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ከ300 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በዚህ በሽታ ይሠቃያሉ። የበሽታው መከሰት በሁሉም ቦታ እየጨመረም ይገኛል። ዲፕረሽን እንደ መንስኤ ወይም ውጤት በመሆን የበሽታ መከላከያዎችን ጨምሮ ብዙ የሰውነት ስርዓቶችን የሚያጠቃ ውስብስብ የስነ-ልቦና እክል ነው። የእንቅልፍ መረበሽ እና የምግብ ፍላጎት ውስጥ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል። በአንዳንድ ሁኔታዎች ክብደት መቀነስ ያስከትላል፣ በሌሎች ውስጥ ለክብደት መጨመር አስተዋጽኦ ያደርጋል። ዲፕረሽን ብዙውን ጊዜ ከጭንቀት ጋር አብሮ ይመጣል። ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በአብዛኛው ሁለቱ ሁኔታዎች አብረው መከሰታቸው ነው። ምልክቶቹ *** ዲፕረሽን ያለባቸው ሁሉም ሰዎች ሁሉንም ምልክቶች ላያሳዩ ይችላሉ። አንዳንዶች ጥቂት ብቻ አንዳንዶች ደግሞ ብዙ የዲፕረሽን ምልክቶችን ሊያሳዩ ይችላሉ። የህመሙ ምልክት ከግለሰብ ግለሰብ እና በጊዜ ሂደት ይለያያል። ዲፕረሽን ብዙውን ጊዜ የማያቋርጥ ሀዘን፣ ጭንቀት ወይም ባዶ ስሜትን ያካትታል። የተስፋ መቁረጥ ወይም የተስፋ ማጣት ስሜት እና የጥፋተኝነት ስሜት፣ ዋጋ ቢስነት ወይም አቅመ ቢስነት እንዲሁም የግብረ ሥጋ ግንኙነትን ጨምሮ በትርፍ ጊዜ ማሳለፊያዎች እና እንቅስቃሴዎች ላይ ፍላጎት ወይም ደስታን ማጣትን ሊያካትት ይችላል። የኃይል መቀነስ፣ የድካም ስሜት ወይም «የዘገየ» ስሜት እንዲሁም እረፍት ማጣት፣ መበሳጨት እና ትኩረትን መሰብሰብ፣ ማስታወስ ወይም ውሳኔ ማድረግ መቸገር የተለመደ ነው። የመንፈስ ጭንቀት ያለባቸው ብዙዎች ስለ ሞት ወይም ራስን ስለ ማጥፋት ያስባሉ። የመንፈስ ጭንቀት ያለባቸው ሰዎች በእንቅልፍ (እንቅልፍ ማጣት፣ በጠዋት መነቃቃት ማጣት ወይም ከመጠን በላይ መተኛት) እና በአመጋገብ ባህሪ (የምግብ ፍላጎት ለውጥ፣ ክብደት መቀነስ ወይም መጨመር) ላይ መስተጓጎል ሊያጋጥማቸው ይችላል። የማያቋርጡ አካላዊ ምልክቶች ደግሞ ራስ ምታት፣ የምግብ መፈጨት ችግር እና ሥር የሰደደ ሕመምን ሊያካትቱ ይችላሉ። የድባቴ (ዲፕረሽን) ምክንያቶች *** ድባቴ ውስብስብ በሽታ ነው። በትክክል መንስኤው ምን እንደሆነ ማንም አያውቅም። ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል። አንዳንድ ሰዎች በከባድ የሕክምና ሕመም ወቅት ድባቴ ያጋጥማቸዋል፣ ሌሎች እንደ መንቀሳቀስ አለመቻል ወይም የሚወዱትን ሰው በሞት ማጣት በመሳሰሉ የህይወት ለውጦች ድባቴ ሊያጋጥማቸው ይችላል። ሌሎች ደግሞ በዘር የሚመጣ ድባቴ ይኖርባቸዋል እናም ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በሀዘን እና በብቸኝነት ሊዋጡ ይችላሉ። የሚከተሉትን ጨምሮ ብዙ ነገሮች በድባቴ የመጠቃት እድልን ይጨምራሉ፤ ጥቃት፦ አካላዊ፣ ወሲባዊ ወይም ስሜታዊ ጥቃት በኋለኛው ህይወትዎ ለድባቴ የበለጠ ተጋላጭ ያደርግዎታል። ዕድሜ፦ በዕድሜ የገፉ ሰዎች ለድባቴ የተጋለጡ ናቸው። እንደ ብቻውን መኖር እና የማህበራዊ ድጋፍ እጦት ባሉ ሌሎች ሁኔታዎች ይበልጥ ሊባባስ ይችላል። አንዳንድ መድኃኒቶች፦ እንደ አይዞሬቲኖይን (ብጉርን ለማከም ጥቅም ላይ የሚውለው)፣ ፀረ ቫይረስ መድኃኒት ኢንተርፌሮን-አልፋ እና ኮርቲሲቶይድ ያሉ አንዳንድ መድኃኒቶች ድባቴን ይጨምራሉ። ግጭት፦ ባዮሎጂያዊ ተጋላጭነት ባለው ሰው ላይ የሚኖር ድባቴ በግላዊ ግጭቶች ወይም ከቤተሰብ አባላት ወይም ጓደኞች ጋር ባለ ያለመግባባት ሊከሰት ይችላል።…

Continue Readingድባቴ/Depression 
Read more about the article ጉልባን እና ሌሎች ዋንኛ ፭ቱ የሰሙነ ሕማማት ሃይማኖታዊና ትውፊታዊ ክንዋኔዎች
የሰሙነ ሕማማት ሃይማኖታዊና ትውፊታዊ ክንዋኔዎች

ጉልባን እና ሌሎች ዋንኛ ፭ቱ የሰሙነ ሕማማት ሃይማኖታዊና ትውፊታዊ ክንዋኔዎች

አብዛኛዎቻችን እንደምናውቀው በዐቢይ ጾም ከሰርክ ሆሳዕና ጀምሮ እስከ ትንሣዔ ሌሊት ያሉት ዕለታት የሚገኙበት ሳምንት ሰሙነ ሕማማት በመባል ይታወቃል። እነዚህ በሰሙነ ሕማማት ውስጥ ያሉት ቀናት የዓመተ ፍዳ እና የዓመተ ኩነኔ መታሰቢያ ናቸው።ታዲያ በእነዚህ ቀናት የተለያዩ ትውፊታዊና ሃይማኖታዊ ክንዋኔዎች ይደረጋሉ። ከነዚህ ክንዋኖዎች ውስጥ ፮ቱን ዋንኛ የሰሙነ ሕማማት ሃይማኖታዊ ትውፊታዊ ክንዋኔዎች አለመሳሳም፣ አክፍሎት፣ ቄጤማ ማሰር፣ ጥብጠባ፣ ጉልባን እና ሕፅበተ እግር በዛሬው ቀን ጸሎተ ሐሙስ እየተባለ በሚጠራውና ጉልባን በሚበላበት ዕለት…

Continue Readingጉልባን እና ሌሎች ዋንኛ ፭ቱ የሰሙነ ሕማማት ሃይማኖታዊና ትውፊታዊ ክንዋኔዎች

«As a Man Thinketh» የሚለው መጽሐፍ 5 ዋንኛ ሐሳቦች

ትርጒም በአብዱልአዚዝ ኑርአዲስ (ኢትዮስታር ተርጓሚ) የምትሆነው ወይም የሚያጋጥምህ የምታስበውን ነው! አሁን ያለህበት ሁኔታ ሊሆን የቻለበት ምክንያት በአንድ ወቅት በነበረህ ወይም አሁንም እያሰብካቸው ባሉ ሐሳቦች ምክንያት የተፈጠረ ሁኔታ ነው። እራስህን መቀየር ከፈለግክ፣ ሐሳቦችህን በመጀመሪያ መቀየር አለብህ። እያንዳንዷ የሰው ልጅ የሚወስዳት እርምጃ መነሻዋ በድብቅ አእምሮ ውስጥ ያሉ ሐሳቦች የዘሯት ዘር ፍሬ ነች። ትክክለኛውን ሐሳብ በመምረጥና ተግባር ላይ በማዋል የሰው ልጅ ወደ ፍጹም መለኮታዊ ደረጃ ሊያድግ ይችላል። የተሳሳተ ሐሳብን ምርጫው ካደረገና ይህንኑ በተግባር ላይ ካዋለው ደረጃው ከአውሬ በታች ሊወርድ ይችላል። መልካምና ቀና ሐሳቦች በጭራሽ መጥፎ ውጤቶችን ሊያስከትሉ አይችሉም፤ መጥፎ ሐሳቦች እና ተግባሮች ፈጽሞ ጥሩ ውጤትን ሊያስገኙ አይችሉም።  አእምሮህ እንደ ዐፀደ አታክልት ነው! የመጽሐፉ ደራሲ አእምሯችንን በዐፀድነት (በቅጽረ አታክልትነት) ይመስሉታል። አእምሯችንን ማበልጸግ ወይም መረን እንዲወጣ መልቀቅ የኛው የራሳችን ምርጫ ነው። በአታክልት ቦታችን ላይ ውብ የአበባ ዘሮችን ካልተከልን ስፍራው በራሱ ያልተፈለጉ አረሞችን ማብቀል ይጀምራል። ልክ አትክልተኛው አላስፈላጊ ተክሎችን (አረሞችን) መንጥሮ እንደሚያስወግዳቸው ሁሉ እያንዳንዱ ግለሰብም ትክክለኛዎቹን የሐሳብ ዘሮች በአእምሮው ውስጥ መትከል፣ መንከባከብና አረሞች ሲከሰቱ ሙሉ በሙሉ እየመነጠረ የማጥፋት ኃላፊነት አለበት። ይህን ስናደርግ ሕይወታችን ውብ እንደሆነ ይቀጥላል። ተቃራኒውን ስናደርግ ደግሞ አረሞቹን ለመመገብ ስለምንገደድ ሕይወታችን ይቃወሳል። ሐሳቦች በአእምሮ ላይ ብቻ ሳይሆን በአካል ላይም ተፅዕኖ ያሳርፋሉ! እንዴት እንደምናስብ እና ምን እንደምናስብ በአእምሮ ላይ ብቻ ሳይሆን በአካላችንም ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያሳርፋል። ሰውነታችን የአእምሯችን ባሪያ ነው። ስለሆነም ታስቦበትም ሆነ ሳይታሰብበት የታሰበ ነገር በቀጥታ ለሰውነታችን ሲደርሰው ሰውነታችን ትዕዛዙን ሳያወላውል  አክብሮ ተፈጻሚ ያደርጋል። የመድሐፉ ደራሲ በቀጣይነት በበሽታ የመያዝ ስጋት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ዞሮ ዞሮ በበሽታው እንደሚያዙ ይናገራሉ። ስለዚህ ጤናማ  መሆን ማለት ሰውነትን ብቻ ሳይሆን የአእምሮ ጤናማነትን በይበልጥ የሚመለከት ጉዳይ ነው። ሐሳቡን መለወጥ ያልቻለ ሰው አመጋገቡን ቢለውጥ ለሰውነቱ ምንም እርባና አይኖረውም። በተመሳሳይ መልኩ በአእምሯችን የሚመላለሱ ሐሳቦች እርጅናን ሊያስከትሉ ይችላሉ። ትንሽ ጊዜ ትኩረት ሰጥተን በዙሪያችን ያሉ ሰዎችን ብንታዘባቸው ፊታቸው በፈገግታ የተሞላ ዕድሜያቸው በዘጠናዎቹ ውስጥ ያሉ አዛውንቶችን እናያለን። በተቃራኒው ገና ዕድሜያቸው  በሠላሳዎቹ አጋማሽ ውስጥ ያሉ ፊታቸው በእርጅና መሥመሮች የተሸበሸበ ያለጊዜያቸው ያረጁ ጎልማሶችንም በዚያው ልክ እናያለን። ማንነትህ በዙሪያህ ባሉ ሁኔታዎች የሚወሰን አይደለም! አንድ ነገር ማግኘት ፈልገህ የማታገኘው የመጣህበት የሕይወት ጎዳና ከሌሎች የተለየ ስለሆነ ወይም ያለህበት አካባቢ አንተን ስለማይፈልግህ ወይም ስላልተቀበለህ መስሎ ከተሰማህ፣ ወዳጄ ሆይ ልብ በል ክፉኛ ስተሃል። ማንነትህ በዙሪያህ ባሉ ሁኔታዎች የሚወሰን አይደለም።  እንዲያውም ከአእምሮህ ውጭ ያለው ዓለም በአንተ ሐሳቦች የሚንሸራሸርበት ውስጣዊው ዓለምህ ይዘወራል እንጂ አይዘወርም። በዙሪያህ ያሉት ሁኔታዎች ምንም ይሁኑ ምን ሁልጊዜም አፀፋ ምላሽ የምትሰጥበትን መንገድ መምረጥ ምርጫው ያንተ ነው። የመምረጥ ሙሉ ነጻነት አለህ። በመሆኑም በቁጥጥርህ ሥር የሆኑት ነገሮች ላይ ትኩረት ማድረግ የተሻለው አፀፋ ምላሽ መስጫ አማራጭ መንገድህ  ነው። መቆጣጠር በምትችላቸው ነገሮች ላይ ስታተኩርና በእነርሱ ላይ መሻሻሎችን ስታደርግ በሕይወት ትግል ውስጥ አሸናፊ እየሆንክ ወደፊት ትቀጥላለህ። ብዙ ሰዎች በዙሪያቸው ያሉ ሁኔታዎችን ለመቀየር ይጨነቃሉ። ይሁን እንጂን ራሳቸውን ለመቀየር ግን ፍጹም ፈቃደኛ አይደሉም። በመሆኑም ዕድሜ ልካቸው በአስጨናቂ መፍትሔ አልባ ሐሳቦቻቸው እንደታሰሩ ሰርክ ይኖራሉ። የምታወስዳቸው እርምጃዎችና ሐሳቦችህ አንድ ላይ በስምረት መጓዝ አለባቸው! አንዳንድ የማኅበረሰብ አንቂ ነን የሚሉ ሰዎች የሚሰብኩት ስብከት ያመንከበት ሐሳብ ሁሉ ወደ ስኬታማነት ይቀየራል የሚል ድምዳሜን ይሰጣል። ይህ አባባል ከስበት ሕግ ጋር እንዲቆራኝ ስለተደረገም ሐሳቡ ለብዙ ሰዎች ይቸበቸብላቸዋል። የአነቃቂ ንግግሮችና ፍልሰፍና አብዮት ፈር ቀዳጅ አብዮተኛ የሆነው ማኅበረሰብ አንቂ ጄምስ አለን የሐሳብ በአእምሮ ውስጥ መኖር ብቻ  በቂ እንዳልሆነ በግልጽ ተናግሯል። ሐሳብ መነሻ ነጥብ ብቻ ናቸው። ስለሆነም ሐሳባችንን ከትክክለኛው መወሰድ ያለበት እርምጃዎ ጋር እንዲጣመር ካላደረግን ያቀድነውን ነገር መቼም ቢሆን አናሳካም። ነገሮች እንዲሆኑልህ መመኘት እና ወደ አንተ እስኪመጡ ድረስ መጠበቅ በምንም ዓይነት መንገድ ላንተ የሚሰጥህ ፋይዳ አይኖረውም። ማንኛውንም የምትፈልገውን ነገር ለማግኘት ወደፊት መጓዝ፣ ትክክለኛውን እርምጃ መውሰድ እና አስፈላጊውን ጥረት ሁሉ ማድረግ  ይኖርብሃል።

Continue Reading«As a Man Thinketh» የሚለው መጽሐፍ 5 ዋንኛ ሐሳቦች

በጀምስ ክሊር የተጻፈው “Atomic Habits” (ጥቃቅን ግን ወሳኝ ልማዶች) ከሚለው መጽሐፍ  የተወሰዱ 10 አንኳር ቁምነገሮች

1. ልማድ ምን ማለት ነው? ልማድ ማለት ብዙውን ጊዜ በነሲብ በተደጋጋሚ የሚፈጸም ድርጊት ነው። መጀመሪያ ላይ እንዲሁ ሲታዩ ቀላልና እዚህ ግቡ የማይባሉ ለውጦች በጊዜ ሂደት አስደማሚ ልዩነትን ይፈጥራሉ። 2. እንዴት…

Continue Readingበጀምስ ክሊር የተጻፈው “Atomic Habits” (ጥቃቅን ግን ወሳኝ ልማዶች) ከሚለው መጽሐፍ  የተወሰዱ 10 አንኳር ቁምነገሮች

የኪሊዮፓትራ የመሪነት ጥበብ፦ ውበቷንና ብልሃቷን እንዴት ለንግሥናዋ እንደተጠቀመችባቸው ማሳያ ነጥቦች

መግቢያ የመሪነት ጥበብ ብዙ ሰዎች እንዲኖራቸው የሚመኙት እጅግ አስፈላጊ ችሎታ ነው። የመሪነት ጥበብ ስንል አንድን የጋራ ግብ ለመምታት እንዲቻል ሌሎችን ከጎን በማሰለፍ በአንድ ልብ እኩል እንዲተጉ ልባቸውን የማሸነፍ ችሎታ ማለታችን…

Continue Readingየኪሊዮፓትራ የመሪነት ጥበብ፦ ውበቷንና ብልሃቷን እንዴት ለንግሥናዋ እንደተጠቀመችባቸው ማሳያ ነጥቦች

ስለምን ሴቶች ከወንዶች ይልቅ ረዥም ዕድሜ ይኖራሉ?

በ Esteban Ortiz-Ospina እና Diana Beltekian ትርጒም በብሩክ በየነ ኦርጂናሌው ጽሑፍ በእንግሊዝኛ ኦገስት 14/ 2018 ተጻፈ ወደ ዐማርኛ መጋቢት 2 ቀን 2015 ዓ.ም. ተተረጐመ በየትኛውም የዓለማችን ክፍል ሴቶች ከወንዶች ይልቅ ረዥም ዕድሜ እንዳላቸው ተረጋግጧል – ይሁንና ዕውነታው ሁልግዜ እንዲህ አልነበረም። ከበለጸጉ አገራት የተገኘው ውሂብ (ዳታ) ሴቶች በ19ኛው ክፍለዘመን ከወንዶች ይልቅ ዕድሜያቸው አጭር እንደነበረ ያሳያል። እንዲህ ከሆነ ታዲያ ዛሬ ምን ተገኝቶ ነው ሴቶች ከወንዶች ይልቅ የተሻለ ዕድሜ ያላቸው? በምን ምክንያት ሴቶች ዕድሜያቸው ከወንዶች ይልቅ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ ሄደ? ማቅረብ የምንችለው ማስረጃ ውስንነት አለው። ያልተሟላ ምላሽ ብቻ መስጠት ነው የምንችለው። ሆኖም ግን ምንም እንኳ እያንዳንዱ ምክንያት ምን ያክል ከባድ ተፅዕኖ እንዳለው በእርግጠኝነት መናገር ባንችልም ሴቶች ከወንዶች ይልቅ ረዥም ዘመን እንዲኖሩ ሥነ ሕይወታዊ (ባዮሎጂካል)፣ ሥነ ባሕሪያዊ እና አካባቢያዊ ሁኔታዎች የየራሳቸውን አስተውዋፅኦ እንዳደረጉ እናውቃለን። የተፅዕኖው ክብደቱ ምን ያክል መሆኑ ከግምት ሳይገባ ከቀደሞው ጊዜ ይልቅ በአሁኑ ዘመን ሴቶች ለምን ከወንዶች ይልቅ ረዥም ዕድሜ እንዳላቸው ቢያንስ በተወሰነ መልኩ በእርግጠኝነት መናገር እንችላለን። ለዚህም ሥነ ሕይወታዊ ያልሆኑ አንዳንድ ቁልፍ ምክንያቶችን መጥቀስ ይቻላል። እንግዲያው እነዚህን ቁልፍ ምክንያቶች ምን እንደሆኑ ለማየት እንሞክር። አንዳንዶቹ በቀላሉና በግልጽ የሚታዩ ናቸው። ለአብነት ወንዶች ከሴቶች ይልቅ ሲጋራ ብዙ ያጨሳሉ። ሌሎቹ ምክንያቶች ደግሞ ውስብስብ ናቸው። ለምሳሌ፣ በበለጸጉት አገራት ከአንድ ክፍለ ዘመን ሴቶችን ይበልጥ ሲያጠቁ የነበሩ በሽታዎች በሕክምናው ዘርፍ በመጣው ዕድገት ምክንያት በሽታዎቹን በቁጥጥር ሥር ማዋል ስለተቻለ የሴቶችን ረዥም ዕድሜ የመኖር ዕድል የዚያኑ ያክል በከፍተና ቁጥር እንዲያሻቅብ አድርጓል። በየትኛውም የዓለማችን ክፍል ሴቶች ከወንዶች ይልቅ ረዥም ዕድሜ ይኖራሉ ከዚህ በታች የሚታየው ቻርት ወንዶችና ሴቶች በወሊድ ወቅት ያላቸውን በሕይወት የመቆየት ዕድል ያሳያል።ለሁላችንም በግልጽ እንደሚታየው ሁሉም አገሮች አግድም ከተሠመረው አካፋይ መሥመር በላይ ናቸው – ይህ ማለት በሁሉም አገሮች ውስጥ ያሉ አዲስ የተወለዱ ሴት ጨቅላ ሕፃናት አዲስ ከተወለዱ ጨቅላ ወንድ ሕፃናት ይልቅ በሕይወት የመኖር ዕድል አላቸው። በሚገርም ሁኔታ ይኸው ቻርት ሴቶች የተሻለ ዕድል በየትኛውም አገር እንዳላቸው እያሳየ በአገራት መካከል ያለው ልዩነት ደግሞ ሰፊ ነው። ሩሲያ ውስጥ ሴቶች ከወንዶች ይልቅ 10 ዓመት የበለጠ ይኖራሉ፤ በብሁታን ደግሞ ልዩነቱ አንድ ዓመት እንኳ አይደፍንም። በበለጸጉ አገራት ሴቶች ያላቸው የተሻለ በሕይወት የመኖር ዕድል መጠኑ ያነሰ ነው አሁን ደግሞ በጊዜ ሂደት እንዴት የሴቶች በሕይወት ረዥም ዕድሜ የመቆየት ዕድል እየተሻሻለ እንደሄደ እንመልከት። ከዚህ በታች ያለው ቻርት እ.አ.አ. ከ 1790 እስከ 2014 ባለው ጊዜ ውስጥ በአሜሪካ ውስጥ የወንዶችና የሴቶች በሕይወት የመቆየት ዕድል እንዴት እንደነበረ ያመላክታል። እዚህ ላይ ሁለት ጉዳዮች ጎልተው ወጥተው ይታያሉ። በመጀመሪያ ሽቅብ ወደ ላይ የሚወጣ አዝማሚያ ይታያል፦ ሁለቱም ወንዶችና ሴቶች በአሜሪካ ውስጥ ዛሬ ላይ ከአንድ ክፍለ ዘመን በፊት ይኖሩ ከነበረው ይልቅ የተሻለ ረዥም ዕድሜ ይኖራሉ። ይህ እውነታ በመላው ዓለም ዙሪያ የሰው ልጅ ዕድሜ ላይ ከታየው ታሪካዊ መሻሻል ጋር የተጣጣመ ነው። በሁለተኛ ደረጃ፣ መጠኑ እየሰፋ የሚሄድ ክፍተት ይታይል፦ ሴቶች ረዥም ዕድሜ የመኖር ዕድላቸው በፊት ላይ በጣም አነስተኛ ነበረ ሆኖም ግን ባለፈው ክፍለ ዘመን በጉልህ በሚታይ ደረጃ መሻሻል አሳይቶ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል። በቻርቱ ላይ የተቀመጠውን ‘አገር መቀየሪያ’…

Continue Readingስለምን ሴቶች ከወንዶች ይልቅ ረዥም ዕድሜ ይኖራሉ?

በዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን ዶ/ር ትምኒት ገብሩን ማሰብ ወደድን

ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን በዓለም ዙሪያ ያሉትን ሴቶች ስኬት ዕውቅና እና ተገቢውን ክብር ለመስጠት የምንጠቀምበት የተለየ ቀን ነው። በያዝነው ዓመት ክብረ በዓሉን የኮምፒውተር ሳይንቲስት እና በአርቴፊሻል አስተውሎት (አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ) መስክ…

Continue Readingበዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን ዶ/ር ትምኒት ገብሩን ማሰብ ወደድን

ጦርነት ያስነሳው የትርጉም ስራ… አድዋ!

የአድዋ ጦርነት  የአድዋ ጦርነት በ19ኛው ክፍለ ዘመን የአፍሪካዋ ኢትዮጵያንና የአውሮፓ ሀያልዋን ያፋጠጠ ታላቅ ታሪክ ቀያሪ ግጭት ሲሆን አፍሪካውያን የአውሮፓን ገዢ ሀይላት በድል እንደ ሀገር ብሎም እንደ አህጉር መመከት የጀመሩበት ምዕራፍ…

Continue Readingጦርነት ያስነሳው የትርጉም ስራ… አድዋ!

ከመፃህፍት የተገኘ ፥ ለጊዜ ተዋቸው!

ከመፃህፍት የተገኘለጊዜ ተዋቸው!በአንድ ትንሽ መንደር ውስጥ የሚኖር አንድ ሰው ነበር። ታዲያ ይህ ሰው፣ በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ በኑሮው ከሚገጥመው ችግር የተነሳ፣ ሁልጊዜም በህይወቱ ደስተኛ አልነበረም። አንድ ቀን ግን ከሚኖርበት ሥፍራ…

Continue Readingከመፃህፍት የተገኘ ፥ ለጊዜ ተዋቸው!

ሁሉም_ነገር_ለበጎ_ነው

አንድ ንጉስ ከአሽከሩ ጋር ለአደን ወደ ጫካ ያመራል። ዙርያውን ወጥመድ በማጥመድ ላይ ሳሉ አንደኛው ወጥመድ የንጉሱን እጅ ላይ አርፎ እጁን ያሳጠዋል። ንጉሱም በመጮህ ላይ ሳለ አሽከሩ የደማውን እጁን በጨርቅ እየጠቀለለ…

Continue Readingሁሉም_ነገር_ለበጎ_ነው

በራስ መተማመን እንዴት እንገነባለን ???

ለአንድ ግለሰብ ከሚያስፈልጉት መሠረታዊ የስነ-ልቦና እሴቶች መካከል አንዱና ዋነኛው በራስ መተማመን (self confidence) ነው፡፡ ብዙዎቻችን በራስ መተማመናችን አነስተኛ ወይም ከነጭራሹ ባለመኖሩ ምክንያት ያጣናቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ ለመሆኑ በራስ መተማመን ምንድን…

Continue Readingበራስ መተማመን እንዴት እንገነባለን ???

ውሸት፣ ለምን እንዋሻለን ?? ውሸት ተናጋሪዎችን እንዴት እናውቃለን??

ክፍል አንድ ሰላም ለእናንተ ውሸትን የተለያዩ ምሁራን ትርጓሜና እና ማብራሪያ ሰጥተውበታል በዚህም ነጋሪውን ለመጥቀም የታሰበ ሐሰታዊ የሆነ ግንኙነት(ሚሼል) የሚለው መጀመሪያው ሲሆን ይህም ብዙ ውዝግቦችን አስነስቶ ነበር፡፡ምክንያቱም ነጋሪውን ብቻ ለመጥቀም ውሸት…

Continue Readingውሸት፣ ለምን እንዋሻለን ?? ውሸት ተናጋሪዎችን እንዴት እናውቃለን??

ሞክሼ ፊደላት

ሞክሼ ፊደላት የሚባሉት አንድ ዓይነት ድምፅ ያላቸው ነገር ግን በቅርጽ እና በሥራቸው የተለያዩ ፊደላት የሆኑ ናቸው። በድሮ ጊዜ ግን አባቶቻችን ሀን ከ ሐ ፣ ጸን ከ ፀ… ፊደሎችን በድምፅ አወጣጥ…

Continue Readingሞክሼ ፊደላት

ሎካላይዝ የሚደረገውን ሶፍትዌር ማዘጋጀት – ክፍል 3

ሎካላይዜሽን ጠቃሚ ያልሆነ እና ብዙ ጊዜ የሚፈጅ ነገር ተደርጎ ይወሰዳል፣ በዚህም ምክንያት ብዙ ድርጅቶች ጊዜው እስኪረፍድ ድረስ ለጉዳዩ ቦታ አይሰጡትም። ሶፍትዌር አዘጋጆቹ ኮዱን ሲያዘጋጁ ለሌሎች ቋንቋዎች፣ ዓለም አቀፋዊ ቅርጾች ወይም…

Continue Readingሎካላይዝ የሚደረገውን ሶፍትዌር ማዘጋጀት – ክፍል 3

የሎካላይዜሽን ሥራ እንዴት መጀመር ይቻላል? ክፍል 2

በአብዛኛው፣ ሶፍትዌርዎትን ወይም ድር ጣቢያዎን ሎካላይዝ ለማድረግ የሚያወጡት አጠቃላይ ወጪ፣ ሥራው ከሚፈጥራቸው ዕድሎች ከሚገኘው ተመላሽ ያነሰ ነው የሚሆነው። ምርትዎትን ወይም አገልግሎትዎትን ሎካላይዝ ለማድረግ ከወሰኑ፣ ምርቱ ወይም አገልግሎቱ ሎካላይዝ ለመደረግ ዝግጁ…

Continue Readingየሎካላይዜሽን ሥራ እንዴት መጀመር ይቻላል? ክፍል 2

ሎካላይዜሽን ለንግድ ሥራ አስፈላጊነቱ ምንድነው? ክፍል 1

1- ሎካላይዜሽን ለንግድ ሥራ አስፈላጊነቱ ምንድነው? የንግድ ሥራ ሲሠራ ሁሌም ቢሆን ወጪዎች ይኖራሉ፣ ሆኖም ግን ከልክ በላይ መሆን የለበትም። ብዙ ድርጅቶች ምርቶቻቸውን ሎክላይዝ ማድረግ ተጨማሪ የአስተዳደር ወጪዎችን የሚያስከትል እና ምርቱ…

Continue Readingሎካላይዜሽን ለንግድ ሥራ አስፈላጊነቱ ምንድነው? ክፍል 1

End of content

No more pages to load