ጦርነት ያስነሳው የትርጉም ስራ… አድዋ!

የአድዋ ጦርነት

 የአድዋ ጦርነት በ19ኛው ክፍለ ዘመን የአፍሪካዋ ኢትዮጵያንና የአውሮፓ ሀያልዋን ያፋጠጠ ታላቅ ታሪክ ቀያሪ ግጭት ሲሆን አፍሪካውያን የአውሮፓን ገዢ ሀይላት በድል እንደ ሀገር ብሎም እንደ አህጉር መመከት የጀመሩበት ምዕራፍ አስጀማሪም ነበር።

     ጣልያን ኢትዮጵያን ከመብት እና ሉአላዊነቷ አራቁታ ለመግዛት ያስችላት ዘንድ በጣልያንኛ ያዘጋጀችው የተጭበረበረው የውጫሌው ውል እንደ መንስኤ የሚቀመጥ ታላቅ የትርጉም መፋለስ የታየበት ሰነድ ነበር።

     ሚያዚያ 25 ቀን 1881ዓ.ም. የተፈረመው የውጫሌ ውል በሁለቱ ሀገራት ወዳጅነትና የንግድ ትስስርን ያመጣል ተብሎ የተጀመረ ነበር። የውሉ የጣልያንኛ ትርጓሜ ከአማርኛው የውሉ ትርጓሜ ጋር በርካታ ልዩነትና አለመተማመን የጫረ ቢሆንም ለግጭቱ እንደ ዋነኛ ምክንያት የሚጠቀሰው የጣልያንኛው ሰነድ አንቀጽ 17 ላይ ጣልያን የኢትዮጵያን የውጭ ግኑኝነት መቆጣጠር የሚያስችላትን ስልጣን መደንገጉ ነው። ይህም ጣልያን በኢትዮጵያ ላይ የማዘዝ ስልጣን ሰጥቶ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት የጣሰ ነበር። ይህ የሁለቱም ሀገራት ግኑኝነት መሻከር ታሪካዊ የሆነውን የአድዋ ጦርነት አስከተለ።

የውጫሌ ውል፡ አንቀጽ 17

አማርኛ፡ “የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ለሚፈልጉት ጉዳይ ሁሉ በኢጣሊያ መንግስት አጋዥነት መላላክ ይቻላቸዋል፡፡”

ጣልያንኛ፡ “የኢትዮጵያ መንግስት ከውጭ አገር መንግስታት ጋር የሚያደርገውን ግንኙነት በኢጣሊያ መንግስት አማካኝነት ማድረግ ይገባዋል፡፡”

የአድዋ ጦርነት አፍሪካዊዋ ኢትዮጵያን አጭበርብሮ ለመግዛት ያቀደው የጣልያን ስሌት የውጫሌውን ውል በአማርኛና ጣልያንኛ የተለያየ ትርጉም መስጠቱ ነበር። ይህም ኢትዮጵያ ግንኙነቱን ወደ መጠየቅ ብሎም ሰነዱን እውቅና ወደ መንሳት በሄዱበት ወቅት የአውሮፓዋ ሀያል ጣልያን ኢትዮጵያ ላይ ጣርነት ማወጇን አስከተለ።

የአድዋው ድል የኢትዮጵያ ጽናትና አልንበረከኬነት ያሳየ የጥቁር ህዝቦች መኩሪያ የአለም ፖለቲካ አቅጣጫ  ለዋጭ የሆነ የመላው አፍሪካውያን ደማቅ ታሪክ ነው።

የአፍሪካውያን መብት አስከባሪው እንቅስቃሴ አስጀማሪው የሆነው የኢትዮጵያውያን ጀግንነት ለራስ መብት የመቆምን ውጤት ያሳየና የትርጉም ስራ ምን ያህል እውነተኝነት፣ ሀቀኝነትና ኃላፊነት የተሞላው ዋናውን ሰነድ በትክክል ማንፀባረቅ ያለበት ስራ ነው። የውጫሌ ውል ይሄንን የትርጉም ስራ ስነምግባር አስፈላጊነት ምሳሌ ነው።

ምንጭ

https://www.britannica.com/event/Treaty-of-Wichale

https://gspi.unipr.it/sites/st26/files/allegatiparagrafo/17-02-2015/documenti_-_treaty_of_wuchale_1889.pdf

https://www.britannica.com/biography/Menilek-II

Leave a Reply