በጀምስ ክሊር የተጻፈው “Atomic Habits” (ጥቃቅን ግን ወሳኝ ልማዶች) ከሚለው መጽሐፍ  የተወሰዱ 10 አንኳር ቁምነገሮች

You are currently viewing በጀምስ ክሊር የተጻፈው “Atomic Habits” (ጥቃቅን ግን ወሳኝ ልማዶች) ከሚለው መጽሐፍ  የተወሰዱ 10 አንኳር ቁምነገሮች

1. ልማድ ምን ማለት ነው?

ልማድ ማለት ብዙውን ጊዜ በነሲብ በተደጋጋሚ የሚፈጸም ድርጊት ነው። መጀመሪያ ላይ እንዲሁ ሲታዩ ቀላልና እዚህ ግቡ የማይባሉ ለውጦች በጊዜ ሂደት አስደማሚ ልዩነትን ይፈጥራሉ።

2. እንዴት ጥሩ ልማድን ማጎልበት እንደሚቻል

ትክክለኛ የልማድ ማስተካከያ እርምጃዎችን ስንወስድ፣ ጤናማ ልማዶችን ማጎልበት ያን ያክል ጥረት የሚያስፈልገው ነገር አይሆንም።

                       1. ፍንጭ – በግልጽ የሚታይ

                       2. ከልብ መሻት – አጓጊ እንዲሆን ማድረግ

                       3. ምላሽ አሰጣጥ – በተቻለ መጠን ቀላል እንዲሆን ማድረግ

                       4. ሽልማት – አርኪ እንዲሆን ማድረግ

3. ውጤቱ ላይ አለማተኮር

ከውጤቱ ይልቅ በጉዞው ሂደት ላይ አተኩር። ደጋግመህ የምታደርገውን በመጨረሻ ውጤት ሆኖ ታገኘዋለህ። ሕይወትህ በአጭሩ ሲታይ የድግምግሞሾች ድምር ውጤት ነው። እውነተኛ የባሕሪ ለውጥ ሲባል ሙሉ በሙሉ ቀደምት ማንነትን መቀየርን ይጠይቃል።

4. አዳዲስ ልማዶችህን አጥብቆ መያዝ

አንድን አዲስ ልማድ ስትጀምር፣ ማለትም ወደፊት የምታደርገውና መቼ እንደምታደርገው ለራስህና ለሌሎች ደጋግሞ መናገር ያልከውን የማድረግ ዕድልህን ይጨምራል። ሌላኛው ፍቱን ዘዴ አሁን ያለ ነባር ልማዳችን ለይተን ካወቅን በኋላ በርሱ ላይ አዲሱን የምንፈልገውን ልማድ መደረብ ነው።

5. ቀረቤታ

መነቃቃት ከሚገባው በላይ ቦታ ተሰጥቶት ይታያል። ከመነቃቃት ወይም በሁኔታዎችና በነገሮች አስገዳጅነት ከመነሣሣት ይልቅ ለለውጥ የምንነሣሣበት ከባቢያዊ ድባብ ይበልጥ ለለውጥ አስፈላጊነት አለው። አዳዲሶቹን ልማዶችህን የሚያግዙ በዓይን ሊታዩ የሚችል ምቹ ከባቢያዊ ድባብን ራስህ ፍጠር። ማናቸውንም አሉታዊ ፈተናዎችን መቋቋም ወይም ማስወገድ በምትችልበት መልኩ እያንዳንዷ ጥረትህን እንዴት እንደምታከናውናት ልዩ ዕቅድ አውጣላት።

6. የመጀመር አስፈላጊነት!

አንድን ነገር ልትካንበት ከፈለግክ ሌላ ምንም ሳይሆን የሚያስፈልግህ በተግባር ነገሩን ማድረግ መጀመር ነው። ይኸው ነው ሌላ ምስጢር የለውም! እንከን አልባ ከሆነ የሚያምር ዕቅድ ይልቅ አንድን jነገር ደጋግሞ ማድረግ ይበልጥ የተሻለ ነው። ብዛት ወደ ጥራት ያደርሳል። ትክክለኛው እዚህ ላይ መጠየቅ ያለበት ጥያቄ “አዲሱን ልማዴ ከኔ ጋር እስከሚዋሃድ ድረስ ምን ያክል ጊዜ ይወስድብኛል?” ሳይሆን “ምን ያክል ጥረት ይጠይቃል?” የሚል መሆን አለበት።

7. ራስን በራስ ተጠያቂ ማድረግ

ልማድን በቅርበት መከታተል፣ ከራስ ጋር ለተገባ ውል ተገዢ መሆን እና አንዳች ጉድለት ሲያጋጥም ራስን በራስ ተጠያቂ ማድረግ አዎንታዊ ልማዶችን ለመገንባት ወይም መጥፎዎቹን ለማስወገድ የሚያስችሉ ፍቱን ዘዴዎች ናቸው። ይህንን ማድረግ እንድትችል የሚያግዙህ በርካታ መተግበሪያዎችን ማግኘት ይቻላል። ይሁን እንጂ የዕለት ተዕለት ድርጊትህን በዕለት ውሎ መዝገብ በእጅህ መጻፉ ተመራጭ ነው።

8. ድብርትን መቋቋም

ታላላቅ የሚባሉ ሰዎችን ከሌሎች የሚለያቸው ድብርትን የመቋቋም ችሎታቸው ነው። ስሜታቸው የፈለገውን ያክል ቢጎዳ ወይም የሆነ ሌላ ነገር የማድረግ ፍላጎት ቢወጥራቸው እንኳ በአቋማቸው ፀንተው ለመቆየት ፈቃደኛ ናቸው። የስኬት ዋንኛው እንቅፋት ድብርት እንጂ በፈተና መውደቅ አይደለም።

9. የግል ጥንካሬና ፅኑ ፍላጎት

ፍላጎቶችህና ችሎታዎችህ ምን እንደሆኑ ጠንቅቀህ ተረዳ። ላንተ ቀላል ለሌሎች ከባድ የሆኑ ነገሮች ምንድን ናቸው? የምታወደውንና የምትደሰትበትን ነገር ማድረግ ስትጀምር ስኬታማነት በጣም ቀላል ይሆናል።

10. ቀጣይነት ያለው መሻሻል፡  ጥሩ ልምዶችን መፍጠር የዕድሜ ልክ ጉዞ ነው። መሻሻልዎን ይቀጥሉ፣ መማርዎን በጭራሽ አያቁሙ።

Leave a Reply