ስለ ድርጅታችን

ኢትዮስታር የሎካላይዜሽን እና ትርጉም አገልግሎት

በ 2013 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ በመደበኛነት የተቋቋመው እና የብዙ ቋንቋዎች አገልግሎት አቅራቢ (MLV) የሆነው ኢትዮስታር የትርጉም አገልግሎት፣ በውስጡ ብቃት ያላቸውን ተርጓሚዎች፣ የሎካላይዜሽን ባለሙያዎች፣ መዝገበ ቃላት አዘጋጆች፣ ፕሩፍሪደሮች፣ ኮፒ ጸሐፊዎች፣ ትራንስክሬተሮች፣ የመተግበሪያ ሶፍትዌር አዘጋጆች፣ የበይነ መረብ ግብይት ባለሙያዎች፣ የኮምፒውተር ፕሮግራመሮች፣ ለድርጅቱ የዕለት ተዕለት ሥራዎች አስፈላጊ የሆኑ የቢሮ እና የድጋፍ ባለሙያዎችን የያዘ ነው።

በአስመራ ኤርትራ፣ ካርቱም ሱዳን፣ ጁባ ደቡብ ሱዳን፣ ናይሮቢ ኬንያ፣ ሞቃዲሾ ሶማሊያ እኛ ጅቡቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶችን ለመክፈት ራዕይ ይዘን እየተንቀሳቀስን እንገኛለን፣ በዚህም በአፍሪካ ቀንድ ያሉትን ሰፊ ባህሎች እና ቋንቋዎች በማስተሳሰር በቀጠናው ቋንቋዎች እና ባህሎች ላይ የሚደረገው የጥበቃ፣ ምርምር፣ የመረጃ አሰባሰብ እና የማጎልበት ሥራ ላይ መሳተፍ እንችላለን።

ስለዚህ ኢትዮስታር በተለይ በአፍሪካ ቀንድ፣ እንዲሁም በአጠቃላይ አፍሪካ ከፍተኛ ጥራት ያለው፣ ሙያዊ እና ተዓማኒ የሆነ የቋንቋ ትርጉም አገልግሎት አቅራቢ ለመሆን በቁርጠኝነት እየሠራ ይገኛል።በቋንቋ አገልግሎት ዘርፍ ውስጥ ቀዳሚ መሆናችንን እና ከፍተኛ የትርጉም ውሂብ፣ እውቀት፣ ሀብቶች እና አገልግሎቶች ላኪ መሆናችንን ለደንበኞቻችንም ለራሳችንም ማረጋገጥ ፍላጎታችን ነው። በሥራችን ደስተኛ የሆኑ ደንበኞቻችን የትርጉም ፍላጎቶቻቸውን በማሟላት ወደ ስኬት የሚያመራው መንገድ ውስጥ ለማስገባት ቃል ገብተናል።

የላቀ ደረጃ ለመድረስ የጋራ ግብ በመያዝ የተነሳን እንደ አጋር በጋራ የምንሠራ የተርጓሚዎች እና አስተርጓሚዎች ስብስብ ነን። የሎካላይዜሽን አገልግሎቶችን ወደ ኢትዮጵያ በማስተዋወቅ ረገድ ፈር ቀዳጅ ድርጅት እንደመሆናችን መጠን ትክክለኛውን ሂደት ከሁሉም ገጽታዎች አንጻር ከመገንባት አንጻር ብዙ መሠራት እንዳለበት እናውቃለን።

እኛን ለምን ይመርጡናል? ከሌላው በምን እንለያለን?

ተርጓሚዎቻችን

  • ደንበኞቻችን ሊሆኑ ለሚችሉ በቀላሉ በሚታይ መልኩ ተርጓሚዎቻችንን የመቅጠር ጠንካራ የብቃት ማረጋገጫ እና የማጣራት ሂደት
  • ከኢትዮጵያ በአዲስ አበባ፣ አሳይታ፣ ድሬዳዋ፣ ጅግጅጋ፣ ሀዋሳ፣ ጅማ፣ እንዲሁም ናይሮቢ (ኬንያ) እና ካምፓላ (ኡጋንዳ) የሚገኙ ከ 100 በላይ ወደ አፍ መፍቻቸው የሚተረጉሙ ወይም የአፍ መፍቻ ያህል ችሎታ ወዳላቸው ቋንቋ የሚተረጉሙ ተርጓሚዎች።
  • ጉልህ አካዳሚክ ስኬት እና ቋንቋዎችን እና ባህሎችን በማስተዋወቅ ረገድ ልዩ ችሎታ ያላቸውን አንጎላዊያን፣ ኤርትራዊያን፣ ኢትዮጵያዊያን፣ ፈረንሳያዊያን፣ ጣሊያናዊያን፣ ኬኒያዊያን፣ ሶማሊያዊያን፣ ሩሲያዊያን እና ኡጋንዳዊያን የቋንቋ ባለሙያዎችን የያዘ ዓለም አቀፍ ድርጅት።
  • ለአታላዮች እና አማተሮች ቦታ የለንም።
  • የሚሰጡንን ሥራዎች ለሌሎች የአገልግሎቱ አቅራቢዎች በመስጠት ኮሚሽን አንወስድም።ለምናቀርባቸው የትርጉም አገልግሎት ቋንቋዎች ሁሉ በድርጅቱ ውስጥ ሆነው የሚሠሩ ተርጓሚዎች አሉን እንዲሁም ተርጓሚዎቻችን በየወሩ የሚከፈላቸው የፍሪላንስ ሠራተኞቻችን ናቸው። እያንዳንዱ የሚሰጠን የትርጉም እና ሎካላይዜሽን ሥራ ተሠርቶ በአግባቡ ለደንበኞች እንዲደርስ የሚያስችሉ በጥሩ ሁኔታ የሠለጠኑ ወደ አፍ መፍቻ ቋንቋቸው የሚተረጉሙ ተርጓሚዎች ጠንካራ ስብስብ የያዘ።

የሥራ ፍሰት ሂደታችን እና የደንበኞች አያያዝ

  • በትርጉም እና ሎካላይዜሽን ሂደት ውስጥ ሊያስፈልግዎ የሚችለውን ነገር ሁሉ ማቅረብ እንችላለን፦በአንድ ቦታ የ ትርጉም፣ ኤዲቲንግ እና ፕሩፍሪዲንግ (TEP)፣ የDTP፣ የድምጽ ቅጂ (voiceover)፣ ስክሪፕት የመጻፍ (scripting)፣ ሰብታይትል የማዘጋጀት (subtitling)፣ ትራንስክሬሽን (trans-creation)፣ ደቢንግ (dubbing)፣ ትርጉሙ ወደሚሠራበት ቋንቋ መረጃ መሰብሰብ እና መተንተን፣ ሶፍትዌር ዴቨሎፕመንት፣ ግራፊክ ዲዛይን፣ በግ ፊክሲንግ እና ትራብልሹቲንግ የሚያገኙበት ሁሉን አቀፍ የሎካላይዜሽን አገልግሎት
  • ባለ 5 ኮከብ ደረጃ የትርጉም ጥራት፦ ፍፁም ጥራት ያለው የሥራ ውጤት የሚመጣው ቀልጣፋ እና ሳይንሳዊ ከሆነ የትርጉም ሂደት፣ ሙያዊ የሆነ የፕሮጀክት አስተዳደር፣ ጥብቅ እና ክትትል የሚደረግበት የትርጉም፣ የፕሩፍሪዲንግ (TEP) አካሄድ፣ እንዲሁም በይዘት ዘርፉ ባለሙያዎች ተሳትፎ ነው።
  • አጠቃላይ እና ጥብቅ QA (የጥራት ግምገማ) ሂደት እና ሥርዓት።
  • አጠቃላይ እና ጥብቅ QA (የጥራት ግምገማ) ሂደት እና ሥርዓት።
  • ለምናስከትላቸው ያልተጠበቁ አደጋዎች እና ስሕተቶች ገንዘብ የመመለስ እና በራሳችን ላይ የምንወስናቸው ቅጣቶች እና የካሳ ክፍያዎች።
  • ለመደበኛ ደንበኞቻችን የተለያዩ ቅናሾች እና የማስተዋወቂያ ቅናሾች።
  • በቀን ለ 24 ሰዓታት በሳምንት ለ ሰባት ቀናት የእርስዎን ፍላጎት ለማሟላት ለመሥራት ፈቃደኛ ነን።
  • የደንበኞቻችንን ፍላጎት ለማስተናገድ ነጻ ተጨማሪ አገልግሎቶችን ለመስጠት ፈቃደኛ ነን።
  • በትኩረት እና ትሕትና የሚሠሩ የደንበኞች አገልግሎት ሠራተኞች።
የምንጠቀማቸው ቴክኖሎጂዎች

ቴክኖሎጂን (ማለትም CAT መሣሪያዎች) በትርጉም ሂደት ውስጥ ለማዋሃድ ባለን አቅም ምክንያት ሁሌም ከተፎካካሪዎቻችን እንለያለን። እንደየሥራው ስፋት እና የደንበኞቻችን ፍላጎት የሚከተሉትን በኮምፒውተር የሚታገዙ የትርጉም መሣሪያዎች (CAT መሣሪያዎች) መጠቀም እንችላለን፦

I. ትርጉም እና የትርጉም ትውስታ መሣሪያዎች
III. መዝገበ-ቃላት ማዘጋጃዎች
II. Localization Tools

የትርጉም እና ሎካላይዜሽን አገልግሎት ከሰጠናቸው ዋና ዋና ደንበኞቻችን መካከል

የኢትዮስታር ተርጓሚዎች እና ሠራተኞች ዜግነት፦