ሞክሼ ፊደላት

ሞክሼ ፊደላት የሚባሉት አንድ ዓይነት ድምፅ ያላቸው ነገር ግን በቅርጽ እና በሥራቸው የተለያዩ ፊደላት የሆኑ ናቸው።

በድሮ ጊዜ ግን አባቶቻችን ሀን ከ ሐ ፣ ጸን ከ ፀ… ፊደሎችን በድምፅ አወጣጥ ይለዮአቸው ነበር።

እኝህ ፊደላት በቁጥር ፱ (9) ሲሆኑ
ሀ ፣ ሐ ፣ ኀ ፣ ሠ ፣ ሰ ፣ አ ፣ ዐ ፣ ጸ ፣ ፀ ናቸው።

ሀ ➺ ሃሌታው “ሀ” ይባላል።
◦ሃሌ ሉያ ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ይህን ፊደል ስለሆነ ሃሌታው “ሀ” ተብሏል።

ሐ ➺ ሐመሩ “ሐ” ይባላል።
◦ሐመር ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው በዚህ ፊደል ስለሆነ ነው።

ኀ ➺ ብዙኀኑ “ኀ” ይባላል
◦ብዙህ ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ይህን ስለሆነ ነው።

አ ➺ አልፋው “አ” ይባላል።
◦አልፋ ኦሜጋ ብለን ስንጽፍ የምንጠቀምበት ስለሆነ ነው።

ዐ ➺ ዓይኑ “ዐ” ይባላል።
◦ዓይኑ ብለን ስንጽፍ የምንጠቀምበት ስለሆነ ነው።

ሠ ➺ ንጉሡ “ሠ” ይባላል።
◦ንጉሥ ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ይሄን ፊደል ስለ ሆነ ነው።

ሰ ➺ እሳቱ “ሰ” ይባላል።
◦እሳት ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ይህን ስለሆነ ነው።

ጸ ➺ ጸሎቱ “ጸ” ይባላል።
◦ጸሎት ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ይሄን ፊደል ስለሆነ ነው።

ፀ ➺ ፀሐዩ “ፀ” ይባላል።
◦ፀሐይ ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ይህን ፊደል ነው።

✅ እነዚህ ሞክሼ ፊደላት አንዱ በአንዱ ቦታ መግባት የለበትም ምክንያቱም የትርጉም ለውጥ ያመጣሉ።
ለምሳሌ ፦
➺ ሠረቀ = ወጣ
ሰረቀ = ሰረቀ
➺ አመት = አገልጋይ
ዓመት = ዘመን
➺ ሰዐለ = ስዕል ሳለ
ሰአለ = ለመነ
➺ መሀረ = አስተማረ
መሐረ = ይቅር አለ
➺ ኀለየ = አመሰገነ
ሐለየ = አሰበ
➺ ፈጸመ = ጨረሰ
ፈፀመ = ነጨ
➺ ማኅሌት = ማመስገን
ማሕሌት = ማሰብ

ምንጭ፦ መሠረተ ግእዝ

Leave a Reply