ሥራዎቻችን

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኤማኑኤል ማክሮ እና የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እንደ ቅምሻ የተሰኘውን የኛን መጽሐፍ ሲመለከቱ ይታያሉ። እንደ ቅምሻ (በበርናር ዱመርሼ አሳታሚ የታተመው መጽሐፍ) የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ለኢትዮጵያው አቻቸው በገጸ በረከት መልክ የሰጡት መጽሐፍ ነው። ይህ የፈረንሳዊው ታላቅ ባለቅኔ አርቲዩር ረምቦ የመጀመሪያው የዐማርኛ ወጥ ትርጒም ሲሆን ረምቦ በኢትዮጵያና በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ ለ10 ድፍን ዓመታት (ከ1881 እስከ 1891 እ.አ.አ) እንደኖረ ይታወቃል። የአርቲዩር ረምቦ ግጥሞችና የሥነ ጽሑፍ ሥራዎች በብሩክ በየነ፣ ፍራንሷ ሞሮ እና ዶ/ር ብርሃኑ አበበ የተተረጐሙ ሲሆን በአለን ሳንሰርኒና ዦን ሚሸል ለዳ አማካይነት አርትዖት ተደርጎባቸዋል። ይህ በሁለት አገራት በሻማ ቡክስ እና በዱመርሼ የታተመው መጽሐፍ በፈረንሳይ ኤምባሲ የገንዘብ ድጋር የተደረገለት ነው።

በዚሁ በተመሳሳይ ወቅት በአለን ሳንሰርኒ እና አርቲስት ጆኤል ሌይክ የተጻፈው Rimbaud selon Harar የሚለው መጽሐፍ በፕሬዝዳንቱ አማካይነት ለኢትዮጵያ ፕሬዝዳንዳት ወ/ሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ ተበርክቶላቸዋል።
N.O.E., 13/03/2019
Photo : le Monde, 12/03/2019

https://www.lemonde.fr/international/article/2019/03/13/a-addis-abeba-macron-veut-que-la-france-porte-le-renouvellement-de-l-ethiopie_5435127_3210.html

Mahlye Ze Kazanchis

መኅልየ ዘካዛንቺስ - Mahlye Ze Kazanchis

ከፍራንሷ ሞሮ ጋር በመተባበር በጃንዋሪ 2008 በL'Archange Minotaure አሳታሚነት ፓሪስ ፈረንሳይ ውስጥ መኅልየ መኅልየ ዘካዛንቺስ ወደ ፈረንሳይኛ ተተርጉሞ ታትሟል።

ስሜት- SEMET

ስሜት- SEMET

ስሜት ("SEMET" / Sensation) በመቅደላዊት ድንቁ የተዘፈነ ዘፈን። የአርቲዩር ረምቦ "Sensation" ግጥም በብሩክ በየነና ፍራንሷ ሞሮ ወደ ዐማርኛ ከተተረጎመው ስሜት የሚለው ግጥም ላይ በመመርኮዝ የተዘጋጀ ሙዚቃ። የሙዚቃው ባለቤት መቅደላዊት ድንቁ። በኦክቶበር 7/ 2012 የተለቀቀ።

እንደ ቅምሻ - Ende Kimsha

እንደ ቅምሻ - Ende Kimsha

“እንደ ቅምሻ” በዐማርኛ በፈረንሳይኛ ደግሞ “Passages” የሚል መጠሪያ የተሰጠው የፈረንሳዊው ታላቅ ባለቅኔ አርቲዩር ረምቦ የሥነ ግጥም መድብል በማርች 2016 ተርጉመን በሻማ ቡክስ (BookWorld) አሳታሚነት፣ አዲስ አበባ ውስጥ እና በጁን 2016 ፓሪስ ውስጥ በ DUMERCHEZ አሳታሚ በኩል ለገበያ እንዲቀርብ አድርገናል።

Arthur Rimbaud Sensation Passage

Sensation, Bohemian

“Sensation”፣ “Bohemian”፣ “Cabre Vert / The Green Inn” የተሰኙ አራት የረምቦ ግጥሞች በተለያዩ ድምፃዊያን መስፍን ማሞ፣ ግሩም ሌሎችም የተዘፈኑ ሲሆን የሙዚቃ ቅንብሩን የሠሩት አማኑኤል ይልማ እና አምባቸው ሲሆኑ ጊዜውም ከላይ በተጠቀሰው መጽሐፍ ምርቃት በማርች 2016 የቀረቡ ነበሩ።

ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን:

ሳማድ በጫካ ውስጥ - Samad in the Forest

ሳማድ በጫካ ውስጥ - Samad in the Forest

“ሳማድ በጫካ ውስጥ” የተባለውን በመሐመድ ኡማር የተባለ እንግሊዛዊ የተጻፈ የሕፃናት መጽሐፍ ተርጉመናል፣ መጽሐፉም በ Salaam Publishing, London, 2019 (ISBN 9781912450237 ) ታትሟል።

ሳማድ ኣብቲ ጫካ - Samad in the Forest

ሳማድ ኣብቲ ጫካ - Samad in the Forest

“ሳማድ ኣብቲ ጫካ” የተባለውን በመሐመድ ኡማር የተባለ እንግሊዛዊ የተጻፈ የሕፃናት መጽሐፍ በተርጓሚያችን በቴድሮስ ማርቆስ አማካይነት ወደ ትግርኛ ቋንቋ ተርጉመናል፣ መጽሐፉም በ Salaam Publishing, London, 2019 (ISBN 9781912450213 ) ታትሟል።

Samaad Bosona Keessa - Samad in the Forest

Samaad Bosona Keessa - Samad in the Forest

“Samaad Bosona Keessa” የተባለውን በመሐመድ ኡማር የተባለ እንግሊዛዊ የተጻፈ የሕፃናት መጽሐፍ በተርጓሚያችን በብርሃኑ ተድላ አማካይነት ወደ ኦሮሚኛ ቋንቋ ተርጉመናል፣ መጽሐፉም በ Salaam Publishing, London, 2019 ታትሟል። (ISBN 9781912450190 )

ሳማድ በበረሃው ላይ - Samad in the Desert

ሳማድ በበረሃው ላይ - Samad in the Desert

“ሳማድ በበረሃው ላይ” የተባለውን በመሐመድ ኡማር የተባለ እንግሊዛዊ የተጻፈ የሕፃናት መጽሐፍ ተርጉመናል፣ መጽሐፉም በ Salaam Publishing, London, 2019 (ISBN 9781912450237 ) ታትሟል። (ISBN 9781912450244 )

ሳማድ ኣብቲ ምድ ረበዳ - Samad in the Desert

ሳማድ ኣብቲ ምድረ በዳ - Samad in the Desert

“ሳማድ ኣብቲ ምድረ በዳ” የተባለውን በመሐመድ ኡማር የተባለ እንግሊዛዊ የተጻፈ የሕፃናት መጽሐፍ በተርጓሚያችን በቴድሮስ ማርቆስ አማካይነት ወደ ትግርኛ ቋንቋ ተርጉመናል፣ መጽሐፉም በ Salaam Publishing, London, 2019 ታትሟል። (ISBN 9781912450220 )

Samaad Gammojjii Keessa - Samad in the Desert

Samaad Gammojjii Keessa - Samad in the Desert

“Samaad Gammojjii Keessa”የተባለውን በመሐመድ ኡማር የተባለ እንግሊዛዊ የተጻፈ የሕፃናት መጽሐፍ በተርጓሚያችን በብርሃኑ ተድላ አማካይነት ወደ ኦሮሚኛ ቋንቋ ተርጉመናል፣ መጽሐፉም በ Salaam Publishing, London, 2019 ታትሟል። (ISBN 9781912450206 )