ሎካላይዜሽን ለንግድ ሥራ አስፈላጊነቱ ምንድነው? ክፍል 1

1- ሎካላይዜሽን ለንግድ ሥራ አስፈላጊነቱ ምንድነው?

የንግድ ሥራ ሲሠራ ሁሌም ቢሆን ወጪዎች ይኖራሉ፣ ሆኖም ግን ከልክ በላይ መሆን የለበትም። ብዙ ድርጅቶች ምርቶቻቸውን ሎክላይዝ ማድረግ ተጨማሪ የአስተዳደር ወጪዎችን የሚያስከትል እና ምርቱ ለገበያ የሚወጣበትን ጊዜ የሚያዘገይ ስለሚመስላቸው ለሎካላይዜሽን የሚውለው ጊዜ ውጤት አልባ ነው ብለው ያስባሉ። ምናልባት ይህ ዕውነት ሊሆን ይችላል ነገር ግን ስኬታማ የሆነ የማስፋፊያ ሥራ መሥራት የእርስዎ ግብ ከሆነ ያለ ሎካላይዜሽን ማሳካት ከባድ ይሆናል፣ ይህም እንደሚያስቡት መጥፎ እንደማይሆን እርግጠኛ መሆን ይቻላል።

ሎካላይዜሽን ለንግድ ሥራዎት ጠቅሚ ከሚሆንባቸው መንገዶች ጥቂቶቹ እንደሚከተለው ቀርበዋል፦

2- የደንበኞችን እርካታ ማሻሻል

ሎካላይዜሽን ቀጥታ ይዘቱን ወደ ሌላ ቋንቋ ከመትርጎም በላይ ነው። ሎካላይዜሽን አንድ ይዘት ከአካባቢው ባህል ጋር ተስማሚ እንዲሆን እና አካባቢያዊ ልማዶችን ማሟላት እንዲችል በጥንቃቄ የማስተካከል እና የማመቻቸት ሂደት ነው። በአብዛኛው ጊዜ ድርጅቶች ዓለምአቀፍ ዘመቻዎችን ለማዘጋጀት በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ወጪ ያደርጋሉ፤ ይህም ሆኖ ግን መፈክሮቻቸው ባልታሰበ ሁኔታ በታለሙባቸው አገራት አስቂኝ ወይም አጸያፊ ዐውድ ወዳላቸው ትርጉሞች ተለውጠው ሲግኙ ይስተዋላል።

ሎካላይዜሽን እንደዚህ ዓይነት ችግር ውስጥ እንዳይገቡ ይረዳዎታል። ለተለያዩ ደንበኞች የበለጠ ማራኪ የተጠቃሚ ተሞክሮ ለማቅረብ ያግዝዎታል፣ ይህም ሲሆን በጠቃላይ ደንበኞችዎት በሶፍትዌሩ ውስጥ እርስዎ የሚፈልጉትን ቁልፍ እንዲጫኑ ለማድረግ ይረዳል።

3- የተጠቃሚ ደንበኞችን ብዛት መጨመር

ዓለም አንድ በሆነችበት በዚህ ወቅት አንድ ድርጅት የተጠቃሚ ደንበኞችን ቁጥር ለመጨመር የሚኖረው አቅም ወሳኝ ነው። ከዚህ ቀደም የነበሩትን ምርቶች ትርጉምን እና የሎካላይዜሽን አስተዳደርን በመጠቀም አመቻችቶ ወደ አዳዲስ ገበያዎች ማስገባት መቻል ዓለም አቀፋዊ ለሆነ ዕድገት ቀልፍ ነው። ሎካላይዝ የተደረጉ ምርቶች ከአካባቢያዊ ገበያ ሁኔታዎች ጋር በተሻለ ሁኔታ መስማማት ስለሚችሉ እንዲሁም የሚኖራቸው ባህላዊ ገደብ አነስተኛ ስለሚሆን  ሙያዊ የሆነ ሎካላይዜሽን ለአዳዲስ ደንበኞች ከምርቱ አኳያ የሚኖረውን ገደብ ለመቀነስ ይረዳል።

ሎካላይዜሽን ብዙ ሸማቾች ስለምርትዎ እንዲያውቁ ለማስቻል እና የተጠቃሚ ደንበኞችን ቁጥር ለመጨመር ያስችልታዎል። ለምሳሌ FAMILO የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያውን ለዓለም አቀፍ ቤተሰቦች እንዲሆን በማድረግ ካሳደገ እና ስኬታማ በሆነ ሎካላይዜሽን አማካኝነት የኢንደስትሪው መሪ ከሆነ በኋላ በአስገራሚ ሁኔታ የአዳዲስ ደንበኞች ምጣኔ በ 400% እንደጨመረ ተመልክቷል።

4- ሎካላይዜሽን ወደ አዳዲስ ገበያዎች በፍጥነት መግባት እንዲችሉ ያስችልዎታል

ሎካላይዝ የተደረጉ ምርቶች ባህላዊ እንቅፋቶችን ማለፍ ስለሚችሉ የሎካላይዜሽን ሂደት ምርቶች አዳዲስ ገበያዎች ውስጥ የሚገቡበትን ፍጥነት ይጨምራል። ይህም ደንበኞች ስለ ምርቱ ለሌሎች የሚናገሩበትን ዕድል እያሰፋው ይሄዳል። ይዘቶቻቸውን ሎካላይዝ የሚያደርጉ ድርጅቶች ከተለያዩ ደንበኞች በኩል የሚኖሩ ተሳትፎዎች እና የገበያ ድርሻዎች አንጻር መሻሻሎችን የማየት አዝማሚያ አላቸው።

ይህ ማለት ከንግድ ሥራ አንጻር ስንመለከተው፣ ምርቶችን ለደንበኞች በፍጥነት እና ተለዋዋጭ በሆነ መልኩ በማድረስ ለተወዳዳሪነት አወንታዊ ጥቅም ማግኘት ነው። በፍጥነት ምርቶቻቸውን ሎካላይዝ ማድረግ የሚጀምሩ ድርጅቶች ዕድገታቸውም በዚያው ልክ ፈጣን ይሆናል፣ ለዚህም ምክንያቱ ግልጽ ነው። ለምሳሌ ያህል፣ 95% ያህሉ የሚታዘዙ የትርጉም ሥራዎች በ 24 ሰዓታት ውስጥ ይደርሳሉ እንዲሁም 80% ያህሉ ትዕዛዞች 12 ሰዓታት ወይም ከዚያ በታች ይወስዳሉ የሚለውን ሐረግ መጠቀም። ይህም ደንበኞቻችን የንግድ ሥራቸውን ወደ አዳዲስ ገበያዎች በጣም በፍጥነት ማስገባት እንዲችሉ ያስችላቸዋል።

እነዚህን ነጥቦች ሁሉ ከግምት በማስገባት፣ የንግድ ሥራዎት ሎካላይዝ የማያደርጉበት ምንም ዓይነት ምክንያት የለም ለማለት ይቻላል እንዲሁም ይህን እያነበቡ ከሆነ ደግሞ በሂደቱ ላይ ፍላጎት አለዎት ማለት ነው። በጣም ሰነፍ ካልሆኑ፣ ባሉበት የመቆየት ሃሳብ ከሌሎት፣ ሽያጮችን ማጣት የሚያስደስትዎ ካልሆነ እና መስፋፋት የማይፈልጉ ካልሆነ በስተቀር፣ ለዚህ ጥያቄ መልስዎት የሚሆነው፦ “አዎ በትክክል” ነው።

የንግድ ስትራቴጂዎ ገቢን፣ የገበያ ድርሻን እና የተጠቃሚ ደንበኞችን ብዛት ማሳደግ ላይ የሚያተኩር ከሆነ፣ ሎካላይዜሽን ለንግድ ሥራዎ አስፈላጊ ነገር ነው። በመሆኑም፣ በእውነቱ የንግድ ሥራዎ እነዚህን ሦስት ነገሮች ከግምት ካላስገባ፣ የንግድ ሥራ ነው ብለው ራሱ መጥራት ይችላሉን?

ጥራቱን የጠበቀ የሎካላይዜሽን አገልግሎት ማግኘት ይፈልጋሉ? በተመጣጣኝ ዋጋ ከ30 በሚበልጡ ቋንቋዎች መተርጎም እንችላለን። በቀጥታ በበይነ መረብ በፍጥነት አገልግሎት እንሰጣለን። ከ70 በላይ የሆኑ በሙያው የሠለጠኑ ተርጓሚዎቻችን አብዛኛዎቹን የኢትዮጵያና ምሥራቅ አፍሪካ ቋንቋዎች ከአብዛኛዎቹ የአውሮፓና የእስያ ቋንቋዎች መተርጎም ይችላሉ።

ለበለጠ መረጃ በ: info@ethiostarlocalization.com ይላኩልን

Leave a Reply